የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የኢትዮ-ጅቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የሀገራቱንና የቀጣናውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ያጠናክራል- ምሁራን

Sep 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2019 (ኢዜአ)፦ በጅቡቲ ዳመርጆግና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከማጠናከር ባለፈ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደት ተምሳሌት መሆኑን ምሁራን ገለጹ።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል በተደረገ አጋርነት የሚተገበር ሲሆን፤ ከአንድ ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር በላይ የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን የመያዝ እና የማስተላለፍ አቅም ይኖረዋል።

ፕሮጀክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ እና የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አሊኮ ዳንጎቴ በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።

በጅቡቲ ዳመርጆግና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የነዳጅ አቅርቦትን በማቀላጠፍ የሎጂስቲክስ ችግሮችን እንደሚያቃልልም ጭምር ነው የተገለጸው፡፡


በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህርና ተመራማሪ ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያና ጅቡቲን የረጅም ዘመን ግንኙነት በማሳደግ የኢኮኖሚ ትስስርን ያጠናክራል።

ፕሮጀክቱ ነዳጅ ለማጓጓዝ ይወስድ የነበረውን ጊዜ በማሳጠር ለነዳጅ የሚወጣውን ወጪ መቀነስ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ዘላቂ የነዳጅ አቅርቦትን በማረጋገጥ አስተማማኝ የኢነርጂ ዋስትናና ዘላቂ አቅርቦት እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ በሎጂስቲክስና በትራንስፖርት ዘርፍ ለሁለቱም ሀገራት ዜጎች ከፍተኛ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።

ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራች መሆኗን ማሳያ እንደሆነም ገልጸዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ዳንኤል ሀንድኖ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ተሰሚነት ያላትና አብሮ በማደግ መርህ እየሰራች መሆኗን ጠቅሰዋል።


ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ አብሮ በማደግ እና በሰጥቶ መቀበል መርህ የምታምን ሀገር መሆኗን በተግባር ያሳየና ለሌሎች ሀገራት ተምሳሌት የሚሆን ስትራቴጂካዊ የልማት እርምጃ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያና ጅቡቲ በኤሌክትሪክ ኃይል፣ በመጠጥ ውሃ፣ በባቡር መስመርና በሌሎች የመሰረተ ልማት ትብብሮች የጋራ ትስስር ያላቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

እንደምሁራኑ ገለጻ፤ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የምትከተለውን ቅድሚያ ለጎረቤት የመስጠት ፖሊሲን የሚያንጸባርቅ ነው።

ፕሮጀክቱ ነዳጅን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ የሚቀንስና በትራንስፖርት መዘግየት የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት ቀጣይነት ያለው የነዳጅ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና የሕዝብ ትስስር ይበልጥ በማጠናከር የቆየውን ወዳጅነት ወደፊት የሚያራመድ ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮ-ጅቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የሀገራቱንና የቀጣናውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ያጠናክራል- ምሁራን

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2019 (ኢዜአ)፦ በጅቡቲ ዳመርጆግና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የ...

Sep 28, 2026

ከመሸመት ወደ ማምረት- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ስኬቶች

የአንድ ሀገር ታላቅነትና የማንሰራራት አቅም የሚለካው በገጠሟት ፈተናዎች ስፋት ሳይሆን፣ እነዚያን ፈተናዎች ወደ ልማትና ዘላቂ ስኬት ለመቀየር በሚወሰዱ ቆራጥ አ...

Sep 24, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት የመቀየር ተግባራት ይጠናከራሉ

ሆሳዕና ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራ አማራጮችን ወደ ውጤት የመቀየር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክል...

Sep 20, 2026

የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ጉዳይ ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማስመለስ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና ቀ...

Sep 18, 2026