🔇Unmute
ነቀምቴ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡- በምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በዘንድሮ የበጋ መስኖ 900 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ የማልማት ስራ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የበጋ መስኖ የስንዴ ልማትን እንደ ዋና የኢኮኖሚና የምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ስትራቴጂ በመቅረጽ በስፋት ስትተገብር ቆይታለች።
ከዚህ ቀደም ስንዴ የሚመረተው በክረምት የተፈጥሮ ዝናብ ላይ ብቻ ተመስርቶ የነበረ ቢሆንም፣በአሁኑ ወቅት የመስኖ ቴክኖሎጂንና አሰራርን በማስፋፋት በበጋ ወቅት በስፋት በማልማት ውጤት እየተገኘ ነው።

በዚህ ረገድ የኦሮሚያ ክልል የዚሁ ግዙፍ ኢንሼቲቭ ዋና የልማት ማዕከል በመሆን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ ዞኖች ከፍተኛ የውኃ ሀብት፣ ሰፋፊና ለም መሬት እንዲሁም ምቹ የአየር ንብረት ያላቸው በመሆኑ ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተመራጭ አካባቢዎች ናቸው።
በዘንድሮው የበጋ ወቅትም በምዕራብ ኦሮሚያ ዞን 900 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ለማልማት የተያዘው እቅድ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።

የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ተወካይ አቶ ኮርሳ ዋቅጅራ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የበጋ መስኖ ልማቱ አርሶ አደሮች ምርታማነታቸውን በማሳደግ የምግብ ዋስትናቸውን የሚያረጋግጡበት በመሆኑ ፋይዳው ከፍተኛ ነው።
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ተግባራዊ የተደረገው የስንዴ ልማቱ ከፍተኛ ውጤት ያስገኘና የአርሶ አደሩንና የወጣቱን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ማረጋገጡን ጠቁመዋል።
የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠልም በዞኑ በ900 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ለማካሄድ ታቅዶ ተግባራዊ ስራ ውስጥ መገባቱን ገልጸዋል።
እስካሁን በየደረጃው በተካሄደው የተቀናጀ እንቅስቃሴ 300 ሺህ ሄክታር መሬት ታርሶና ለስልሶ በዘር እየተሸፈነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
ልማቱን ለማሳለጥ የእርሻ ትራክተሮችን ጨምሮ አስፈላጊው የምርጥ ዘር እና የማዳበሪያ ግብዓት በበቂ ሁኔታ ቀርቧል ነው ያሉት።

በምግብ ራስን ለመቻል የተያዘውን አቅጣጫ ለማሳካት የስንዴ ልማቱን በጥራት፣ በፍጥነትና በስፋት የማካሄዱ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተወካዩ አስታውቀዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው አርሶ አደር አለማየሁ ዋቅቶላ በሰጡት አስተያየት፤ በአሁን ወቅት በበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት በማካሄድ የተሻለ ምርት በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘንደሮም ከአካባቢያቸው አርሶ አደሮች ጋር በመቀናጀት በ12 ሄክታር ይዞታቸው ላይ በኩታ ገጠም ስንዴን በማልማት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሌላኛው አርሶ አደር በላይ ሂካ በበኩላቸው፤ ለልማቱ ስኬታማነት ቀድመው በኩታ ገጠም በማረስ እና በቂ ግብዓት በማሟላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
የመስኖ ውሃ አጠቃቀምን በማሻሻልና የተሻለ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ በመጠቀም የስንዴ ምርማነታቸውን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰሩ መሆኑንም አስታውቀዋል።
እንደ አርሶ አደሮቹ ገለፃ በበጋ መስኖ ልማት ከክረምቱ የተሻለ የስንዴ ምርት እያገኙ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የጉቶ ጊዳ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርናና መሬት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ሙላቱ በበኩላቸው፣ በወረዳው በዘንድሮው ዓመት ከ18 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ በስንዴ ለማልማት መታቀዱን ገልጸዋል።
አሁን ላይ የዘር ስራው በተደራጀ አግባብ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው ለመስኖ ምቹ በሆኑ የወረዳው ቀበሌዎች ልማቱን ለማስፋፋት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
ሚዛን አማን፣ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቅዳሜና እሑድ ገበያ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የግብይት ማዕከ...
Nov 4, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር )በሌሎች አካባቢዎች የታየው ፈጣንና ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ በመቐለ ...
Nov 3, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለማስተሳሰር የምታደርገው...
Oct 26, 2026
ጎንደር ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል ሲሉ የአካ...
Oct 20, 2026