የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያን ዕዳ ከሀገራዊ ጥቅል ምርት ያለውን ድርሻ ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል - ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)

Jan 14, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ጥር 6/2017(ኢዜአ)፦በለውጡ ዓመታት በተወሰዱ እርምጃዎች የኢትዮጵያን ዕዳ ከሀገራዊ ጥቅል ምርት ያለውን ድርሻ ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሯ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤቶችና ቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መንግሥት ከለውጡ በፊት የነበሩ የስርዓትና መዋቅራዊ ችግሮችን ለማስተካከል አዲስ የኢኮኖሚና ማህበራዊ የፖሊሲ ዕይታን መከተሉን ገልጸዋል።

ይህ የልማት ፖሊሲ ዕይታ ብዝኃ ዘርፍን ያማከለ፣ የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነት ጥያቄ ምላሽ መስጠት ላይ ቀዳሚ ትኩረት ያደረገና አካታች ስርዓትን ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ግብርና፣ አምራች ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ኢኮኖሚ እኩል የእድገት ምንጭ እንዲሆኑ ትኩረት መሰጠቱንና የኢኮኖሚ ተዋንያን ሚዛን መጓደል እንዲስተካከል መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ ይዞት የቆየውን ጉልህ ሚና ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሥራ መከናወኑንም ነው የገለጹት፡፡

የልማት ፖሊሲዎቹ የዘመናት ችግር ሆኖ የቆየውን መዋቅራዊ ሽግግር ለማሳካት ግብ መያዛቸውንም አስረድተዋል፡፡

በመጀመሪያው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በተተገበረው ፖሊሲ ኢኮኖሚውን ማዘመንና ለውድድር ክፍት ማድረግ ላይ መጠነ ሰፊ ሪፎርም መደረጉን ነው ያነሱት።

ለዚህም የንግድ ህጉንና የኢንቨስትመንት አዋጁን ጨምሮ ከ80 በላይ ህግጋት መቀየራቸውን ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ የአገልግሎት፣ የንግድና ኢንቨስትመንትን ምህዳርን ያሻሻሉና ዲጂታል ኢኮኖሚን እውን ያደረጉ ስኬቶች መመዝገባቸውንም ገልጸዋል።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማና ትርፋማ ከማድረግ ባሻገርም በአዲሱ የፖሊሲ ዕይታ ለዓመታት ለግሉ ዘርፍ ዝግ የነበሩ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ያሉ ግዙፍ ድርጅቶች ክፍት መደረጋቸውን አንስተዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የመንግሥት ገቢን ከማሳደግ፣ የወጪ አስተዳደርን ከማስተካከል፣ በጥናት ላይ የተመሰረተ የፕሮጀክት ትግበራና አፈጻጸምን ከማሻሻል፣ ድጎማን ለታለመለት ዓላማ ከማሸጋገር አንጻር አመርቂ ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቅሰዋል።

በተለይም የመንግሥት ገቢ ከለውጡ በፊት ከነበረበት በብዙ እጥፍ ማደጉን በማሳያነት አንስተዋል።

ከለውጡ በፊት የኢትዮጵያ ልማት ፋይናንስ የተደረገበት መንገድ ሀገር በዕዳ ቀንበር እንድትማቅቅ ያደረገ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ ባለፉት ስድስት ዓመታት ይህንን ለማስተካከል በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ምንም ዓይነት የንግድ ብድር ባለመፈጸም፣ ከአበዳሪዎች ጋር የዕዳ ሽግሽግ በማድረግና፣ ብድርን በከፍተኛ ሁኔታ በመክፈል የዕዳ ጫናውን ማቃለል ተችሏል ብለዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ አሁን ያለባት የዕዳ ጫና ከሀገራዊ ጥቅል ምርት ያለው ድርሻ 13 ነጥብ 7 በመቶ መድረሱን ነው የገለጹት። ከለውጡ በፊት ከ30 በመቶ በላይ እንደነበር በማውሳት።

ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ነው ያስታወቁት።

ለአብነትም የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር፣ ገቢ፣ የወርቅና የቡና የውጭ ገበያ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይ ከፍተኛ ውጤት ማምጣቱን አንስተዋል።

አሁን ላይ ባንኮች ከሚሸጡት የውጭ ምንዛሬ ይልቅ የሚገዙት ከፍተኛ ብልጫ ማሳየቱን ተናግረዋል።

የብሔራዊ ተቀማጭ መጠን በ200 በመቶ ማደጉን ገልጸው፥ የኢንቨስተሮች የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ መፈታቱንም ነው ያነሱት።

ማሻሻያው ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር መንግሥት ለደመወዝ፣ ለነዳጅ፣ ለመድሃኒት ፣ ለሴፍትኔትና ሌሎች ድጎማዎች ከ400 ቢሊዮን ያላነሰ በጀት መመደቡን ገልጸዋል።

መንግሥት የታለመለት የነዳጅ ድጎማን ቢያስቀጥልም በቅርቡ የዓለም የነዳጅ ዋጋንና የውጭ ምንዛሬ ለውጡን መሰረት በማድረግ የዋጋ ማስተካከያ ማድረጉን ጠቁመዋል።

አሁንም ኢትዮጵያ ነዳጅን ከዓለም ገበያ ከ20 እስከ 26 ብር ቅናሽ በማድረግ እየሸጠችና እየደጎመች መሆኗን ነው ያስታወቁት።

መንግሥት ድሃ ተኮር ፖሊሲ የሚከተል በመሆኑ ድጎማዎቹን ውጤታማ ለማድረግ እየሠራ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ የነዳጅ ግብይት ስርዓትን ዲጅታላይዝ ማድረግ፣ ኮንትሮባንድን መቆጣጠርና ነዳጅ በአግባቡ ለተጠቃሚዎቹ መድረሱን ማረጋገጥ ላይ አዳዲስ አሰራሮች እንደሚተገበሩ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025