
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 21/2017(ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፍ አጋሮች ስርዓተ ምግብን ለመደገፍ የገቧቸውን ቃሎች በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲቀይሩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ አሳሰቡ።
ኢትዮጵያ ከጣልያን እና ከተመድ ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው ሁለተኛው የምግብ ስርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር አፍሪካ የምግብ ስርዓት ለውጥ ለማምጣት ጠንካራ የተግባር እርምጃዎችን እየወሰደች እንደምትገኝ ተናግረዋል።
በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካዳፕ)፣ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና እና ዘላቂ፣ ሁሉን አቀፍ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ስርዓት ለመገንባት ስራ 40 ቢሊዮን ዶላር ሀብት የማሰባሰብ ግብ ይዛ እየሰራች መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ፣ እኩልነት የሰፈነበት እና ሁሉን አካታች የምግብ ስርዓትን ለመፍጠር እየተደረገ ያሉ ጥረቶችን የበለጠ ማፋጠን፣ የተገቡ ቃሎችን ወደ ሚለኩ ውጤቶች መቀየር እና የተጠያቂነት ስርዓትን ማስፈን እንደሚገባ አመልክተዋል።
ዓለም አቀፍ አጋሮች የገቧቸውን ቃሎች በተግባር መፈጸም እንዳለባቸው ጠቅሰው የፋይናንስ ተደራሽነት ማሳደግ እና አፍሪካ መር የሆኑ ስራዎችን መደገፍ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል፣ የምግብ ዋስትና እና የዜጎችን የኑሮ ሁኔታን ጨምሮ አፍሪካ ቅድሚያ ከምትሰጣቸው ጉዳዮች ጋር ማጣጣም እንደሚገባቸውም ነው ያሳሰቡት።
ዓለም አቀፍ አጋሮች የገባችሁትን ቃል ኪዳን ወደ ተግባር ቀይሩ ሲሉም ተናግረዋል።
የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽንን ውጤታማ ለማድረግ ጠንካራ አህጉራዊ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ ጠቅሰው ሀገራት ስራቸውን ከአፍሪካ ህብረት ማዕቀፎች እና ኢኒሼቲቮች ጋር ማስተሳሰር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ሀገራቱ በግብርና፣ በስርዓተ ምግብ እና ለአደጋዎች የማይበገር ጠንካራ መሰረተ ልማት መገንባት ስራዎች የሚያፈሱትን መዋዕለ ንዋይ ማሳደግ አለባቸው ነው ያሉት።
በምግብ ስርዓት ፖሊሲ ቀረጻ እና ትግበራ ውስጥ ወጣቶች እና ሴቶችን ዋንኛ ተሳታፊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑንም እንዲሁ።
የምግብ ስርዓት ሽግግር ማድረግ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የሞራል ግዴታ እና ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ጉዳይ እንደሆነም አንስተዋል።
የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ረሃብን ለማጥፋት፣ ድህነትን ለመቀነስ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አቅም ግንባታ ቁልፍ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ
#ኢትዮጵያ
#ምርታማነት
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026