የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

Sep 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ አትክልት አሳቤ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለዘመን መለወጫ በዓል በበቂ መጠን የእርድ እንስሳት፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች መቅረባቸውን ገልጸዋል።

ምርቶቹን ከኢንዱስትሪዎች፣ ከግብርና አምራቾች፣ ከኢንተርፕራይዞች፣ ከህብረት ሥራ ማህበራት እንዲሁም ከእንስሳትና አሳ ሀብት ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።


በተለይም በትላልቅ ከተሞች በተገነቡ 2ኛ ደረጃ የገበያ ማዕከላት፣ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለሸማቹ በቀጥታ እንዲቀርብ መደረጉንም አስረድተዋል።

በበዓሉ ወቅት የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይኖር ቀደም ብሎ በቂ ዝግጅት በመደረጉ፣ ህብረተሰቡ በአቅራቢያው እንዲገበያይ መደረጉንም ነው ያብራሩት።

እስካሁን ባለውም ከ700 ሺህ በላይ የደለቡ ዳልጋ ከብቶች፣ በጎችና ፍየሎች እንዲሁም ከሁለት ሚሊዮን በላይ የስጋ ዶሮዎች ለበዓል ገበያ እንዲቀርቡ ተደርጓል ነው ያሉት።

በተጨማሪም ከ3 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት፣ ከ25 ሚሊዮን በላይ እንቁላል እና ከ34 ሚሊዮን ሊትር በላይ የወተት ምርት ለገበያ ማቅረብ መቻሉን አመልክተዋል።


በዓሉን አስመልክቶ በሁሉም ምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የክልሉ ህብረት ሥራ ኮሚሽን የግብይት ትስስር ባለሙያ አቶ ፈንታሁን ወርቅዬ፤ የግብርናና የፍጆታ ምርቶች በዩኒየኖች፣ በሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት እና በሁለተኛ ደረጃ የገበያ ማዕከላት በኩል እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል።

ለበዓሉ ከ16 ሺህ ኩንታል በላይ ሽንኩርትና ጤፍ፣ 4 ሺህ 500 ኩንታል የዳቦ ዱቄት፣ ከአንድ ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት፣ እንቁላልና የወተት ተዋጽኦዎች ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።


በሁሉም ዘርፍ በቂ የምርት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ የበዓል ገበያ ግብይት እየፈጸሙ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ ስለናት ይዘንጋው ናቸው።

የዋጋ ንረትን ለመቋቋም መንግስት በየአካባቢው የጀመረውን የ2ኛ ደረጃ የገበያ ማዕከላትን የማስፋፋት ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026