
ደሴ ፤ ሐምሌ 23/2017(ኢዜአ)፦ጥቁር አፈር መሬትን በማንጣፈፍ እና ቴክኖሎጂን ተጠቅመው በሚያከናውኑት የግብርና ልማት ሥራ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን የደቡብ ወሎ ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ።
የዞኑ ግብርና መምሪያ በበኩሉ በዘንድሮ ክረምት ከ96 ሺህ ሄክታር በላይ ጥቁር አፈር መሬትን አጠንፍፎ ለልማት በማዋል ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።
በዞኑ ጃማ ወረዳ ቀበሌ 06 ነዋሪ አርሶ አደር ኡመር ሁሴን ለኢዜአ እንደገለጹት የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና አዳዲስ አሰራሮችን ተጠቅመው በሚያከናውኑት የግብርና ሥራ ምርታማነታቸው እያደገ መጥቷል።

ውሃ በመቋጠር ከምርት ውጭ የነበረ አንድ ሄክታር የሚጠጋ ጥቁር አፈር መሬታቸውን ዘንድሮ በማንጣፈፍ እና ቴክኖሎጂ ተጠቅመው በስንዴ መዝራታቸውን ገልጸው፣ ከልማቱም ከ40 ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት የስንዴ ሰብል ቡቃያው ያማረ መሆኑን ጠቁመው፣ ምርታማነታቸውን በማሳደግ ከራስ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተግተው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በግብርና ባለሙያዎች ምክር ጥቁር አፈር መሬታቸውን በማንጣፈፍ ለልማት በማዋል ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደቻሉ የገለጹት ሌላው የእዚሁ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር መከተ ከተማው ናቸው።

ዘንድሮም ውሃ የሚቋጥር ግማሽ ሄክታር ጥቁር አፈር ማሳቸውን አጠንፍፈው ስንዴና ጤፍ በመዝራት ተገቢውን እንክብካቤ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
"በመሬቱ ላይ የሚተኛን ውሃ በማንጣፈፍ የተለያየ ሰብል በማልማት ምርታማ መሆን ችለናል" ያሉት ደግሞ የወረኢሉ ወረዳ ቀበሌ 04 ነዋሪ አርሶ አደር ሲሳይ ደምሴ ናቸው።
ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንድ ሄክታር ተኩል መሬታቸውን አጠንፍፈው በመዝራታቸው ቀደም ሲል ከ20 ኩንታል በታች የነበረውን ምርት ወደ 35 ኩንታል ለማሳደግ መቻላቸውን ተናግረዋል።
ያገኙትን ጥቅም ዘላቂ ለማድረግም ዘንድሮ መሬቱን በማጠንፈፍ እና ቴክኖሎጂና አዳዲስ አሰራሮችን በመጠቀም ስንዴና ጤፍ መዝራታቸውን ገልጸዋል።
የጃማ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀይሉ አሰፋ በበኩላቸው በወረዳው በመኸር ከሚለማው 42 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ 32 ሺህ ሄክታር የሚሆነው ጥቁር አፈርን በማንጣፈፍ የሚለማ መሆኑን ተናግረዋል።

አብዛኛው ጥቁር አፈር መሬት በስንዴ እንደሚለማ ጠቁመው፣ ምርታማነትን በአማካይ በሄክታር 46 ኩንታል ማድረስ ተችሏል ብለዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ይመር ሰይድ በበኩላቸው በዞኑ ውሃ የሚቋጥር 96 ሺህ ሄክታር ጥቁር አፈር መሬትን በማንጣፈፍና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በዘር እየተሸፈነ ነው።
"ቀደም ሲል መሬቱ ውሃ ስለሚቋጥር ሰብሉ እየቀጨጨና ቢጫ እየሆነ ተገቢውን ምርት አይሰጥም ነበር" ያሉት ቡድን መሪው አጠንፍፎ የመዝራት ቴክኖሎጂ ከመጣ ወዲህ አርሶ አደሩ ምርታማነትን ማሳደግ ችሏል ብለዋል።
በተጠነፈፈው መሬት ስንዴ፣ ጤፍ፣ ባቄላና ምስር እንደሚለማ ጠቁመው ይህም ምርታማነትን ከእጥፍ በላይ ለማሳደግ ያስችላል ብለዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን በተያዘው የመኸር ወቅት 432 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት ከ15 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026