የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቀጣናዊ ፎረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Mar 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2018 (ኢዜአ)፦ በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል።

ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ እያሳደረ ባለው ከፍተኛ ተጽእኖ ምክንያት የቀጣናው የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እና የዜጎች የኑሮ መሰረት አደጋ ላይ በወደቀበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል።

ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።


በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ።

በቀጣናው የሥርዓተ ምግብ ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል።

የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ተብሏል።

ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው 

አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...

Jun 10, 2026

በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...

Jun 9, 2026

በፓርኩ ለአቮካዶ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርት የሚያቀርቡ ማህበራት ተጠቃሚ ሆነዋል

ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...

Jun 6, 2026

የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ ያነቃቃል

ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...

May 28, 2026