🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስደናቂ የልማት ዕድገት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለትውልድ የማስረከብ ትልም ፍሬ እያፈራ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ እና ተጋባዦች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመዲናዋ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ የልማት ስኬቶች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻነትን እያሳደገ ነው።
የዓለም ሶስተኛዋ የዲፕሎማሲ ማዕከል የአፍሪካ መዲናና ውቧ አዲስ አበባ የአህጉሪቷ የመግቢያ በርነትን በፍጥነት እያሳደገች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባን ምቹና ተወዳዳሪነት ለማሳለጥ በተገነቡ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች ውስጥ የነዋሪዎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንደተሰጠው አስረድተዋል።
በመዲናዋ በመሠረተ ልማት መስክ የተመዘገቡ ውጤቶችም የበለጸገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ትልም ፍሬ እያፈራ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጠን ለማሳለጥ የተወሰዱ ርምጃዎች ኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት የስበት ማዕከል እያደረጋት እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ የአዲስ መሶብ የዲጂታል የአንድ ማዕከል ለአልሚ ባለሃብቶች የተሳለጠ የመንግስት አገልግሎት የሚያገኙበትን አስቻይ ምኅዳር መፍጠሩንም ገልጸዋል።
የአዲስ አበባን ፈጣን ዕድገት በማሳለጥ ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢን በመፍጠር የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ እያበረታታ መሆኑን አንስተዋል።
የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት ፎረም የመዲናዋን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለማሳየት ገንቢ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያና ጣሊያን ወዳጅነት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ የሀገራቱ ታሪካዊ ወዳጅነትም የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብርን በማጠናከር ከፍተኛ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ አንስተዋል።
በንግድና ኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ አልሚ ባለሃብቶች ድጋፍና ትብብር እንደሚደረግ ጠቅሰው፤ የጣሊያን ባለሃብቶች ዕድሉን እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026