🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ሕገ ወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለመግታት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ ባለፉት አራት ወራት ከአስራ አምስት ቀናት የሕግ ማስከበር እና የቁጥጥር ሥራዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ነዳጅን ጨምሮ በመዲናዋ የሸቀጦች ግብይትን ያለደረሰኝ የሚፈጽሙ ህገ ወጥ ነጋዴዎችና ሕገ ወጥ የደላላ እንቅስቃሴዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የሕግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሊዲያ ግርማ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በመዲናዋ የሕገ ወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለመግታት የተሰሩ ሥራዎች ውጤት እያመጡ ነው።
እንዲያም ሆኖ አሁንም ነዳጅን በጄሪካን ጨምሮ በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰቦች እጅ መኖሩን መለየቱን ገልጸው፤ ሕገ ወጥ የነዳጅ ዝውውር ላይ የሚደረገው ቁጥጥር ይበልጥ ይጠናከራል ብለዋል።
ሰላምና ጸጥታ፣ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ፖሊስና የንግድ ቢሮ ቅንጅታዊ አካሄድ ከበፊቱ በላቀ መልኩ ሊተገበር እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የቁጥጥር ሥራው በዘመናዊ መልኩ እንዲካሄድ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም አመልክተዋል።
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ተስፋዬ ደንድር በበኩላቸው፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተደረገ ቁጥጥርና ክትትል 50 ሺህ 942 ሊትር ናፍጣ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙን ገልጸዋል።
በተመሳሳይም 8 ሺህ 974 ሊትር ቤንዚን በቁጥጥር ሥር ውሏል ያሉት ኃላፊው፤ 35 ግለሰቦችም በሕግ እንዲጠየቁ መደረጉን ተናግረዋል።
ተሽከርካሪዎች ላይ ተጨማሪ ሳልቫቲዮ በመግጠም በሕገ ወጥ መንገድ ነዳጅ ማዘዋወር፣ የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲሁም የቁጥጥር ሥራው ወጥ አለመሆን በውስንነት ከሚጠቀሱ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል እንደሚገኙበት አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት የለም።
እጥረቱ ሰው ሰራሽ ነው ያሉት ኃላፊዋ፤ በምሽት የሚሸጥ ነዳጅ ላይ የተቀናጀና ጠንካራ የቁጥጥር ሥራ ይጠይቃል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮም በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ነዳጅ አቅራቢዎች ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲገቡ የማወያየት ሥራዎች በሰፊው እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ እንደተናገሩት፤ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴን ለመግታት ዘላቂው መንገድ በሕገ ወጥ ተግባር ላይ የሚሰማሩትን ግንዛቤ በማስጨበጥ መመለስ ነው።

ሕግን አለመዋቅ ከተጠያቂነት አያድንም ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ በሕገ ወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት ወደ ሕጋዊ መስመር ሊገቡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጥበቡ ደጀኔ (ዶ/ር) በሰጡት አስተያየት፤ ተጨማሪ ሳልቫቲዮ የተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎች በሕገ ወጥ መንገድ ነዳጅ እንደሚያዘዋውሩ በቁጥጥርና ክትትል ተለይቷል።
ቁጥጥሩ ከነዳጅ ማደያዎች ባለፈ ተሽከርካሪዎች ላይ ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸው፤ መንደሮች ውስጥም ጭምር በተጠናከረ መልኩ ሊካሄድ ይገባል ብለዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዳንኤል ጥላሁን እንደገለጹት፤ በክፍለ ከተማው ነዳጅ ማደያዎች በአግባቡ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ክትትል እየተደረገ ነው።
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025