🔇Unmute
ሐረር፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል የነዳጅ አቅርቦቱ በቁጠባና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መሰረት ባደረጉ መልኩ እየተሰራጨ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር ገለጹ።
በክልሉ የሚቀርበውን ነዳጅ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ በክልሉ የተቋቋመው ስትሪንግ ኮሚቴ ውይይት አድርጓል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ሮዛ ኡመር፤ በውይይት መድረኩ ላይ እንዳሉት በክልሉ የነዳጅ ስርጭትና አጠቃቀሙ በተቀመጠው የመፍትሄ አቅጣጫ መሰረት ይቀጥላል ብለዋል።
ለዚህም ኮሚቴው በትኩረት መስራት እንዳለበት አስገንዝበው የሚቀርበው ነዳጅ በቁጠባና ትኩረትን የሚሹ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መሰረት አድርጎ መሆን እንዳለበት አጽኖት ሰጥተዋል።
በክልሉ የተቋቋመው ግብረ ሃይል የክትትልና ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበው፤ በህገ ወጥ ተግባር ላይ የሚሳተፉ ካሉ የተጠናከረ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ያልተገባ የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ በሚያደርጉ አሽከርካሪዎችና ከነዳጅ ጋር ተያያዥነት ሳይኖራቸው በሸቀጦችና በምርቶች የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ በተመሳሳይ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
በመንግስት ተቋማት የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀሙ የማድረግና በነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚከናወኑ የነዳጅ ግብይቶች የቁጥጥር ሰራ እየተተገበረ መሆኑንም ተናግረዋል።
በምድረኩ የተገኙት የግብረ ሃይል አባላቱ በመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ በነዳጅ አቅርቦት ላይ የፈጠረውን ችግር ለመቋቋም የተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንና እየተከናወኑ የሚገኙ አሰራሮችን በአግባቡ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሊያደርስ የሚችለውን ተጽዕኖ እንዲሁም መንግሥት የሚከተላቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች በተመለከተ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወቃል።
በተለይም ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም፣ የታዳሽ ኃይል አማራጮችን የመጠቀም ልምድ፣ የእግር ጉዞ ባህልን ማጎልበት፣ የሕዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም፣ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ማጋለጥ እና ሌሎችም ከህብረተሰቡ የሚጠበቁ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን አፅኖት ሰጥተዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026