የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በኢሉባቦር ዞን በሙዝ ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ ነው

Jun 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

መቱ፣ ሰኔ 2/2018 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን በሙዝ ልማት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችና ወጣቶች፣ ከምርቱ የሚያገኙት ገቢ እየጨመረ በመምጣቱ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መሆኑን ገለጹ።

በዶረኒ ወረዳ የኤና ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ጌታቸው ወርቅነህ፤ ከአራት ዓመት በፊት አነስተኛ መሬት ላይ ሙዝ ማልማት መጀመራቸውን ይናገራሉ።

በአሁኑ ወቅት የሙዝ ችግኝ እያበዙ መሆናቸውን የገለጹት አርሶ አደሩ፣ ልማቱን ወደ ግማሽ ሄክታር መሬት በማስፋት በሚያገኙት ገቢ ኑሯቸውን ማሻሻል መቻላቸውን ገልጸዋል።


ዘመናዊ የሙዝ አመራረት ዘዴዎችን በመጠቀም የምርት ጥራትና መጠናቸውን ማሳደግ በመቻላቸው ገቢያቸው በተሻለ ሁኔታ እያደገ መሆኑን ጠቁመው፤ ባለፈው ዓመት ከችግኝና ከምርት ሽያጭ እስከ 600 ሺህ ብር ገቢ ማግኘታቸውንና በዚህ ዓመትም የተሻለ ገቢ እንደሚጠብቁ አስረድተዋል።

የሙዝ ልማት ስራው ልጆቼን ለማስተማርና የተሻለ ሕይወት ለመምራት አግዞኛል ያሉት አርሶ አደር ጌታቸው፤ ወደፊት ልማቱን ይበልጥ በማስፋፋት ወደ ኢንቨስትመንት የመሸጋገር እቅድ እንዳላቸውም አጋርተዋል።


የአርሶ አደር ጌታቸውን ስኬታማ ተሞክሮ በመቅሰም በወረዳው የሚገኙ በርካታ ወጣቶች በፍራፍሬ ልማት ለመሰማራት ተነሳስተዋል።

የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወጣት ወንድሙ ለገሰ እና ወጣት አዲሱ ያሲን ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር በመደራጀት በአንድ ሄክታር መሬት ላይ የሙዝ ችግኝ መትከል መጀመራቸውን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ወጣት አዲሱ እምሩ እና ወጣት ምሬሳ ደረጄ በበኩላቸው፤ በሙዝ ልማት ላይ ጠንክረው በመስራት ተጠቃሚ ለመሆን መነሳታቸውን ጠቁመው፣ በተለይም የሙዝ ልማቱን ከሌሎች ጥምር የግብርና ስራዎች ጋር በማስተሳሰር ለማከናወን ማቀዳቸውን ተናግረዋል።


የዶረኒ ወረዳ ግብርናና መሬት ልማት አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ለሊሴ አመና እንደገለጹት፤ በወረዳው ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የግብርና ኢኒሼቲቮች መካከል የፍራፍሬ ልማት አንዱ ነው።

በአሁኑ ወቅት የፍራፍሬ ልማቱ በየቀበሌው በኩታ ገጠም አሰራር እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ ከ1 ሺህ 600 ሄክታር በላይ መሬት በማኅበር በተደራጁ ወጣቶችና በአርሶ አደሮች እየለማ ይገኛል ብለዋል።

የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተመዘገበ ያለውን ውጤት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም ኃላፊዋ አረጋግጠዋል።


የኢሉአባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኜ ፍቅሬ በበኩላቸው፤ በዞኑ በዚህ የክረምት ወቅት ከ29 ሺህ 100 ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች የሚሸፈን ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 4 ሺህ 300 ሄክታሩ በሙዝ ችግኝ የሚሸፈን መሆኑን አስታውቀዋል።

በዞኑ በአሁኑ ወቅት ሙዝን ጨምሮ አቮካዶ፣ አናናስ፣ ፓፓያና ሌሎች የፍራፍሬ ዓይነቶች በስፋት እየለሙ እንደሚገኙም ምክትል ኃላፊው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026