🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ):- የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የፍየልና በግ የእንስሳት ሃብት ዝርያን የሚያሻሽሉ ሙያተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በዚህም ኢንስቲትዩቱ ከሰኔ 08 እስከ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሰው ሰራሽ ማዳቀል የፍየልና በግ የእንስሳት ሃብት ዝርያን ለማሻሻል ለሙያተኞች የሰጠውን ስልጠና በማጠናቀቅ ሰልጣኞችን አስመርቋል።
የግብርና ሚንስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የእንስሳት ሃብት ያላት ሀገር ናት ብለዋል።
የኢትዮጵያን የፍየልና በግ የእንስሳት ሃብት ምርታማነትን ለማሻሻልም የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችንና የአሰራር ሥርዓቶችን በመቅረፅ እየተሰራባቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የፍየልና በግ የእንስሳት ሃብት ምርታማነትን ለማሻሻል እየተሰራበት የሚገኘው የሰው ሰራሽ ማዳቀል ሥነ-ዘዴ ተጨባጭ ውጤት እየተገኘ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩትም የሰው ሰራሽ ማዳቀል ሙያተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት መሰረት መጣሉን አንስተዋል።
በኢንስቲትዩቱ ትምህርትና ስልጠና የተሰጣቸው ሙያተኞችም የእንስሳት ሃብት ምርታማነትን በማሻሻል ህዝባቸውን ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አስራት ጤራ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት የገጠር ሽግግርን ለማሳለጥ ለእንስሳት ሃብት ምርታማነት ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
በዚህም የመንግሥትን መርህ ታሳቢ በማድረግ በሰው ሰራሽ የማዳቀል ሥነ-ዘዴ የፍየልና በግ የእንስሳት ሃብት ምርታማነትና ጤንነት ሙያተኞችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ለምርቃት ለበቁት ሰልጣኝ ሙያተኞችም በእንስሳት እንክብካቤና አመጋገብ፣ በሽታ መከላከልና ጤና አጠባበቅ፣ ምርት ማቀነባበሪያና የገበያ ትስስር ትምህርት መሰጠቱን አስረድተዋል።
በስልጠናውም የያቤሎ፣ ጂንካ፣ ባኮ፣ አዳሚቱሉ፣ የዓርባ ምንጭ ምርምር ማዕከላት፣ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት እንዲሁም የግል እርሻ ሙያተኞች መሳተፋቸውን አስረድተዋል።
#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026