🔇Unmute
ሰመራ፣ ሐምሌ 2/2018(ኢዜአ)፡-በአፋር ክልል እየተከናወነ ያለውን የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ይበልጥ ለማሳደግ ስልጠና ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር መሆኑን በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ኤክስቴንሽን የእንስሳት በሽታ ቁጥጥር ኤክስፐርት አቶ ጌታሁን እንዳለ ገለጹ።
የግብርና ሚኒስቴር ከአፋር ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር፤ በወረዳ ደረጃ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ለተሰማሩና በማህበራት ለተደራጁ 200 ለሚሆኑ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በሰመራ እየሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መድረክ የተገኙት የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ኤክስቴንሽን የእንስሳት በሽታ ቁጥጥር ኤክስፐርት አቶ ጌታሁን እንዳለ፤ ሥልጠናው የዘርፉ ባለሙያዎች ዘመናዊ ዕውቀትንና ቴክኖሎጂን አቀናጅተው ሥራቸውን በብቃት እንዲመሩ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
በእንስሳት እርባታና ጤና ጥበቃ ዘርፍ በማህበራት ተደራጅተው እየሰሩ የሚገኙ ባለሙያዎች በኤክስቴንሽን የተደገፈ አሰራር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የሀገርን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እንዲያስችላቸው ስልጠናው ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት ቢኖራትም አሁን ላይ የሚስተዋለውን አነስተኛ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ፤ የዘርፉን ባለሙያዎችና በማህበራት የተደራጁ ወጣቶችን ክህሎት ማሳደግ እንዲሁም የሚደረግላቸውን ድጋፍ ማጠናከር እንደሚገባም አቶ ጌታሁን አስረድተዋል።
ሀገሪቱ ያላትን እምቅ የእንስሳት ሀብት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፤ በተለይም በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚከናወኑ ተግባራትን ማጠናከርና ባለሙያውን በማብቃት በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።
የአፋር ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ የኤክስቴንሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሞሚና መሐመድ በበኩላቸው፤ በክልሉ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየታዩ መሆኑን ገልጸዋል።

ሥልጠናው ባለሙያዎች ያሉባቸውን ክፍተቶች በመሙላትና አሠራራቸውን በማሻሻል የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የጠቆሙት ዳይሬክተሯ፤ ይህም የልማት ጣቢያ ሠራተኞች ሞዴል አርብቶ አደሮችን ለማፍራት የሚያደርጉትን ጥረት ከማገዝ ባለፈ የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ትግበራ በስኬት እንዲታጀብ ያግዛል ብለዋል።
በክልሉ የአመጋገብ ባህል ለውጥ እየመጣ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሯ፤ ማኅበረሰቡ ዶሮና እንቁላል ከማርባት ባለፈ ለምግብነት መጠቀም መጀመሩን ጠቅሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ በሚገኙ ሁለት ሰው ሠራሽና ስምንት ተፈጥሯዊ ሐይቆች ላይ የተደራጁ ወጣቶች ዓሳ ማምረት መጀመራቸውንና ኅብረተሰቡም ቀስ በቀስ የዓሳ ተጠቃሚነትና የአመጋገብ ባህሉን እያሳደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
ስልጠናው ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆይ መሆኑም ተመላክቷል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026