የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በክልሉ የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታ ለሚያጎለብቱ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷል

Jul 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅግጅጋ፤ ሐምሌ 13/2018(ኢዜአ)፦በሶማሌ ክልል የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚያጎለብቱ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ አስታወቁ።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የክልሉን ኢኖቬሽን ማዕከል መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።


ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በክልሉ የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማጎልበት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና የዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳለጥ ትኩረት ተሰጥቷል።

በዚህም የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው የክልሉ የኢኖቬሽን ማዕከልም በቴክኖሎጂ ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት እና በዘርፉ አቅማቸውን ለማጠናከር ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።

መንግሥት ለቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት የሰጠው ትኩረት አበረታች ለውጦች እያስመዘገበ መሆኑን ጠቁመው ይህንኑ ለማስፋት እየተሠራ ነው ሲሉ አክለዋል። በቀጣይም ማዕከሉን የማስፋት፣ በግብአትና፣ በሙያተኞች የማጠናከር ስራ በትኩረት እንደሚከናወን አመላክተዋል።


የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ መሀመድ አሊ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አቅም የሚገነባና ክህሎታቸውን የሚያጎለብት መሆኑን ተናግረዋል።

ማእከሉ የ2030 የዲጂታል እቅድ ስትራቴጂን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ጠቁመው ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የተቋቋመ መሆኑን ተናግረዋል።


ማዕከሉ በድረገጽ ልማት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በመረጃ ትንተና፣ ሳይበር ሴኩሪቲ፣ ዲጂታል ዲዛይን አገልግሎት በመሳሰሉት ስልጠና የሚሰጥበት መሆኑን ተናግረዋል።

ማዕከሉ በተጨማሪም አነስተኛ ንግዶችን የማልማትና የምርምር አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል።

በስነ ስርአቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ ወጣቶች፣ የፈጠራ ባለሙያዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026