🔇Unmute
ሐዋሳ፤ ሃምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም የተቀናጀና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም እየተገነባ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራርና የድጋፍ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የሲዳማ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራርና የድጋፍ ማስተባበሪያ ኮሚሽነር ሃይሉ ሃሰና፤ በክልሉ ለአደጋ ዝግጁ ከመሆንና ፈጣን ምላሽ ከመስጠት አንፃር እየተደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በማብራሪያቸውም በክልሉ ለአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማጠናከር ከሜቲዎሮሎጂ ኤጄንሲ፣ ከፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ጋር ጠንካራ ትብብር በመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም የምርት አቅምን በማሳደግ ለአደጋዎች ፈጣንና የተሟላ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት ከማድረግ ባለፈ የቅድመ ማስጠንቀቂያና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል ብለዋል።
የዘንድሮው የበልግ ዝናብ በአንዳንድ አካባቢዎች በአግባቡ ያልተዳረሰ በመሆኑ በተለይም የበቆሎ ምርት ላይ ችግር በመፍጠሩ በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ሰብሎችን በመዝራት ለማካካስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ለምግብ እጥረት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየትም በሌማት ትሩፋትና ሌሎችም የግብርና ኤንሸቲቮች ምርታማ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
የመጠባበቂያ እህል ክምችት አቅምን የማሳደግ እንዲሁም የሰብል ልማትና የመጠባበቂያ ፈንድ የማሰባሰብ ጥረት በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉን ተናግረዋል።
በሲዳማ ህዝብ ዘንድ በሚታወቀው ''ፎጮ'' የተሰኘ ባህላዊ ስርአት አማካኝነት ያለው ለሌለው እህል የማሰባሰብ ልምድም ተግባራዊ እየሆነ ነው ብለዋል።
ለአደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የመጠባበቂያ ፈንድ መኖሩን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ በተያዘው ዓመትም ተጨማሪ የመጠባበቂያ ፈንድ የማሰባሰብ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።
እንደ አጠቃላይ በሲዳማ ክልል የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም የተቀናጀና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም እየተገነባ ይገኛል ብለዋል።
በባለፈው ክረምት የወንዝ ሙላት፣ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ያስከተለውን አደጋ መነሻ በማድረግ ለተመሳሳይ አደጋዎች በስጋት አካባቢ የሚኖሩ ወገኖችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች የማስፈር ስራ መሰራቱን አንስተዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026