🔇Unmute
አምቦ፤ ሐምሌ 16/2018(ኢዜአ)፦ አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻሉ የእንስሳት መኖ የሳር ዝርያዎችን በማባዛት ለአርሶ አደሮች ተደራሽ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ጉደር ማሞ መዘመር ካምፓስ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር አማን ሪቂቱ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ተግባሩ ጎን ለጎን በምርምር የተገኙ ዝርያቸው የተሻሻለ የእንስሳት መኖ የሳር ዝርያዎችን በማባዛት ለአርሶአደሩ ተደራሽ እያደረገ ነው ።
ዩኒቨርሲቲው የሳር ዝርያዎቹን በቶኬ ኩታዬ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ የአካባቢው አርሶአደሮች ተደራሽ በማድረግ የእንስሳት እርባታና ማድለብ ስራውን እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው በሶስት ሄክታር መሬት ላይ አስር አይነት የተሻሻለ የእንስሳት መኖ የሳር ዝርያዎችን እያባዛ ለአርሶአደሮች እያሰራጨ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው ጉደር ማሞ መዘመር ካምፓስ የከብቶች ጤና ባለሙያ ዶክተር ጫሉማ ነገራ ናቸው፡፡

የሳር ዝርያዎቹ በውስጣቸው ሀይል ሰጭ እና ገንቢ ንጥረ ነገሮችን የያዙና ለእንስሳት እድገትና ጤና እንዲሁም የወተትና የስጋ ምርትን ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል ።
የሳር ዝርያዎቹ በተጨማሪም ከአካባቢው አየር ጠባይ ጋር የተላመዱና ከእርጥብነት በተጨማሪ በድርቆሽነት ለመኖነት የሚያገለግሉ በመሆናቸው በከብት እርባታና ማድለብ ስራ የተሰማሩ አካላትን ውጤታማ የሚያደርጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ዩኒቨርሲቲው የሳር ዝርያዎቹን እስከአሁን 100 ለሚሆኑ የአካባቢው አርሶ አደሮች በማሰራጨት ልማቱ እንዲስፋፋ ማድረጉን ጠቁመው በቀጣይ ተደራሽነቱን ለማስፋት የበለጠ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
በምዕራብ ሸዋ ዞን የቶኬ ኩታዬ ወረዳ ነዋሪ አርሶአደር ተፈራ ትርፌ፤ ከዚህ ቀደም በተሰማሩበት የወተት ላሞች እርባታ የመኖ አቅርቦት እጥረት ይገጥማቸው እንደነበር አስታውሰዋል ።

አሁን ላይ ከዩኒቨርሲቲው ያገኙትን የተሻሻለ የሳር ዝርያ በማልማትና በመጠቀም የመኖ እጥረትን ከመቅረፍ ባሻገር የወተት ምርታማነትን ማሳደጋቸውን ተናግረዋል።
አሁን ላይ ከአንድ ላም በቀን በአማካይ 12 ሊትር ወተት በማግኘት ገቢያቸውን ማሳደጋቸውን ጠቁመው ከወተት ሽያጭ በሚያገኙት ገቢ መኖሪያ ቤት መገንባታቸውን እና ልጆቻቸውን እያስተማሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026