🔇Unmute
ጋምቤላ፤ ሀምሌ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ7 ሺህ 98 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን የክልሉ ማዕድን ቢሮ አስታወቀ።
የጋምቤላ ክልል ማዕድን ቢሮ ኃላፊ አቶ ቻም ኡበንግ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
በበጀት ዓመቱ 6 ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ለማድረግ ታቅዶ ከ7 ሺህ 98 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።
በክልሉ በበጀት ዓመቱ ገቢ የተደረው የወርቅ ምርት ከእቅዱ በ1 ሺህ 98 ኪሎ ግራም ብልጫ ያለው ሲሆን ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ በ1 ሺህ 669 ኪሎ ግራም ብላጫ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
ለተመዘገበው ውጤት መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የቁጥጥር፣ የክትትልና የድጋፍ ስራዎች ተጠናክረው በመከናወናቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ በበጀት ዓመቱ በተከናወነው የማዕድን ሃብት ልማት ከ6 ሺህ 890 በላይ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል የተፈጠረላቸው መሆኑንም የቢሮ ሃላፊው ገልጸዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026