የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን  ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ የልማት ፍላጎትን ለማሟላት የተጀመሩ ጥረቶች ይጠናከራሉ 

Jul 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አርባምንጭ፤ ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ) ፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ የልማት ፍላጎትን ለማሟላት የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።


የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤት እየተገኘ ነው ።

በተያዘው የ2019 በጀት አመትም የክልሉን የገቢ አቅም ለይቶ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ የግብር እቅድን ለማሳካት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በዚህም በበጀት አመቱ የታቀደውን 48 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

የህግና የአሠራር ስርአት በመታገዝ የገቢ አቅምን በማስፋት የክልሉን ዕድገት ዘላቂነት በማረጋገጥ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ዓለምነሽ ደመቀ በበኩላቸው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በገቢ ራስን ለመቻል በተደረጉ ጥረቶች አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።


ባለፉት ዓመታት በየዓመቱ 7 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የገቢ ዕድገት መመዝገቡን ጠቅሰው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 32 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል።

ተቋማዊ የመፈጸም አቅም በማሳደግና ብልሹ አሠራርን በማስወገድ የገቢ ስራው በዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ መሠራቱን ገልጸዋል።

በ2019 የበጀት ዓመት የክልሉን ወጪ 75 በመቶ በውስጥ አቅም ለመሸፈን የታቀደውን ግብ ለማሳካት በቅንጅት እንደሚሠራ የቢሮ ሃላፊዋ አመልክተዋል።

በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሮች የስራ ሃላፊዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026