የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በክልሉ የቡና ምርታማነትን በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ከፍ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቷል

Jul 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሚዛን አማን፣ ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ):- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቡና ልማትን በማስፋፋትና ምርታማነትን በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከፍ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ገለጸ።

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ ኮጁአብ ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ ከቡና የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከፍ ለማድረግ ልማቱን የማስፋፋትና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል።


በዚህም በክረምቱ ወራት ከ25 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኞችን ለመትከል ወደስራ መገባቱን ተናግረዋል።

የቡና ልማቱን ለማሳካት ዝርያቸው የተሻሻሉና ለደጋና ቆላማ አየር ንብረት ተስማሚነታቸው በምርምር የተረጋገጡ ችግኞች ለአርሶ አደሩ መሰራጨታቸውን ጠቁመዋል።

የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለምርት የሚደርሱ እና ከነባሩ የቡና ዝርያ በእጥፍ ምርት የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቅሰው ልማቱን ለማሳካትም ሙያዊ ድጋፋና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።


በሸካ ዞን የየኪ ወረዳ አርሶ አደር ሰሎሞን ብርሃኔ ከቡና የሚያገኙትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያላቸውን የቡና ማሳ በየዓመቱ እያስፋፉ መሆኑን ገልጸዋል።

አምና ከወረዳው ያገኙትን አንድ ሺህ "ኬ1" የተሰኘ ምርጥ የቡና ችግኝ መትከላቸውንና ዘንድሮም ተግባሩን በማስቀጠል አንድ ሺህ ችግኞችን ለመትከል እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።


ነባሩን የቡና ዝርያ በምርምር በተገኙ የቡና ዝርያዎች እየተኩ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ አርሶ አደር ጢሞቴዎስ ከሮ እና ታደሰ እጅጉ ናቸው።

ቡናን ከማልማት ባሻገር ጥራቱን ለማስጠበቅ በግብርና ባለሙያ ትምህርት ታግዘው እየሠሩ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ያላቸው ማሳ ላይ በየዓመቱ አዳዲስ ችግኞችን እየተከሉ የቡና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ትኩረት መስጠታቸውን ገልጸዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 614 ሺህ ሄክታር መሬት በቡና እየለማ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026