የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በዘላቂ ሰላምና ልማት ስራዎች ሚናችንን እናጠናክራለን-የመንግስት ሰራተኞች

Aug 11, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ገንዳውኃ፣ ነሃሴ 4/2018 (ኢዜአ):- ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ልማትን አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚከናወኑ ተግባራት ሚናቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች ገለጹ።

የከተማው አስተዳደር ከመንግስት ሠራተኞች ጋር በሰላም፣ ጸጥታ እና በልማት ስራዎች ዙሪያ ምክክር አካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የተሳተፉ የመንግስት ሰራተኞች በከተማው በሚከናወኑ በዘላቂ ሰላምና ልማት ስራዎች ሚናቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።

ከሰራተኞች መካከል አቶ በረከት ገብሬ እንደገለጹት፣ ሰላምን በዘላቂነት ማረጋገጥ ለልማት ስራዎች መፋጠን ወሳኝ ነው ።

ሰላምን በዘላቂነት በማረጋገጥ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ዳር ለማድረስ በሚከናወኑ ተግባራት ሚናቸውን እንደሚያጠናክሩ አመልክተዋል ።

"የመንግስት ሰራተኛው የህብረተሰቡ ግንባር ቀደም አገልጋይ እንደመሆኑ መጠን፣ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ እና የጸጥታ ስጋቶችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ አርአያነታችንን ማሳየት አለብን" ብለዋል።

ከድጃ ሙሳ በበኩላቸው፣ የህዝቡን የአገልግሎት ፍላጎት በታማኝነትና በጥራት ማሟላት ለሰላም መረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።

"በየመሥሪያ ቤታችን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ለዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ ​አበርክቷችንን እናጠናክራለን ብለዋል ።


​የገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ አዳነ ሀሰን በበኩላቸው፣ በከተማ አስተዳደሩ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ የሰራተኛው ተነሳሽነት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

​የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በየደረጃው በመፍታት፣ ሰላምን የሚያጽኑና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያፋጥኑ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።


የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ በወቅቱ እንዳሉት፣ የመንግስት ሰራተኛው የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዎችን ግንባር ቀደም መሪ ሆኖ ሊፈፅም ይገባል።

በተለይም ሰላምን በዘላቂነት የማረጋገጥ ስራ የሁሉም መሰረት መሆኑን አመልክተዋል ።

​ሰራተኛው ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት በመስራት የሰላም አምባሳደር ሊሆን እንደሚገባ እና ለአካባቢው ደህንነት መጠበቅ የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026

ባለፉት አምስት ዓመታት አዲስ አበባን የሰላምና የልማት ማዕከል ማድረግ ተችሏል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት አምስት ዓመታት ስር የሰደዱ ችግሮችን በመቅረፍ አዲስ አበባን የሰላምና የልማት ማዕከል ማድረግ መቻሉን የአዲስ...

Jul 18, 2026

በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሁሉም ዘርፍ ለትውልድ የሚሻገር የላቀ ዕድገት እያስመዘገበ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሁሉም ዘርፍ ለትውልድ የሚሻገር የላቀ ዕድገት እያስመዘገ...

Jun 24, 2026