🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 12/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እና ምርታማነትን ለማሳደግ በሌማት ትሩፋት፣ በመስኖ ስንዴ እና አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች ትኩረት በመስጠት ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኗን የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ።
የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት የግብርና ትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ግምገማ እና ከ2026 እስከ 2035 የሚተገበረውን የካምፓላ ድንጋጌ ማዕቀፍን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የሁለት ቀናት መድረክ ተጠናቋል።

የግብርና ሚኒስትር አማካሪ ዜና ሀብተወልድ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።
ሀገሪቱ የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ በሌማት ትሩፋት፣ በመስኖ ስንዴ እና አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች ላይ ትኩረት በመስጠት ስኬታማ መሆኗን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ በአጀንዳ 2063 የተቀመጠውን የበለጸገች አፍሪካን የመፍጠር ርዕይ ለማሳካት የሚያስችሉ ሥራዎችን በቁርጠኝነት እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል።

በመሆኑም አህጉራዊ አቅጣጫዎችን ከሀገራዊ እቅዶች ጋር በማጣጣም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ ለማሳደግ እና የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል።
በምሥራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) የፖሊሲና የምግብ ዋስትና ኤክስፐርት ሲልቪያ ሄንጋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ማዳረስና አቅሙን መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ሀገራዊ እና ቀጣናዊ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እሴት መጨመር እና በድህረ-ምርት አስተዳደር እንዲሁም አህጉር አቀፍ የንግድ ትስስርን ማጠናከር ላይ ልዩ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ሕፃናት እና እናቶች የተመጣጠነ ምግብና አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን እንዲያገኙ መሥራት ወሳኝ መሆኑን አንስተው፣ አባል ሀገራት የግብርና ሥርዓቱን ለማሻሻል በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት አምስት ዓመታት ስር የሰደዱ ችግሮችን በመቅረፍ አዲስ አበባን የሰላምና የልማት ማዕከል ማድረግ መቻሉን የአዲስ...
Jul 18, 2026