የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በበዓል ገበያ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች በቂ አቅርቦት በመኖሩ የተረጋጋ ግብይት እያካሄድን ነው -ሸማቾች

Sep 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ፣ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ):- በሀዋሳ ከተማ ለዘመን መለወጫ የበዓል ገበያ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች በቂ አቅርቦት በመኖሩ የተረጋጋ ግብይት እያካሄዱ መሆናቸውንሸማቾች ገለጹ ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የአዲስ አመት ዘመን መለወጫ በዓልን ታሳቢ ያደረገ አማራጭ የግብይት ማዕከላትን በማመቻቸት በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር ማድረጉን አመልክቷል፡፡


ኢዜአ በከተማዋ በተለያዩ አከባቢዎች ተዘዋውሮ እንተደመለከተው የግብርናም ሆነ የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋት የቀረቡ ሲሆን በተመቻቹ አማራጭ የገበያ ማዕከላት ነዋሪዎች የበዓል ግብይታቸውን እያካሄዱ ናቸው።


አስተያየታቸውን ከሰጡት ሸማቾች መካከል ወይዘሮ መቅደስ ካሳሁን አስተዳደሩ ባመቻቸው የአማራጭ ግብይት ማዕከላት በቂ የሆነ የፋብሪካና የኢንደስትሪ ምርት አቅርቦት መኖሩን ጠቅሰዋል።


በገበያው ከመደበኛው የበዓል ቅናሽ ዋጋ በመኖሩ ሸቀጦችን በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በከተማዋ የግብርናም ሆነ የኢንዱስትሪ ምርቶች በጥሩ ሁኔታ በመቅረባቸው የዋጋ ሁኔታም የተረጋጋ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላው ሸማች አቶ ኢሳያስ ከበደ የተባሉ ናቸው ።


በመደበኛው ገበያና በአማራጭ የግብይት ማዕከላት በማህበራት በኩል ምርቶቻቸውን ማቅረባቸው ሁሉም እንደአቅሙ መሸመት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።

አስተዳደሩ ባመቻቸው የመሸጫ ቦታ ከመደበኛው ገበያ በቅናሽ ለሸማቹ እየሸጡ መሆኑን የተናገረችው ደግሞ ወይዘሪት ብሩክ ቃሬሶ ነች።


የአዲስ ዘመን የበዓል ገበያ የተረጋጋ መሆኑን የተናገሩት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ አጋና ነቶ ለዚህም የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች የላቀ ሚና መጫወታቸውን ተናግረዋል።

የበዓል ገበያውን የተረጋጋ ለማድረግ በምርት አቅርቦትና የዋጋ ቁጥጥርና ክትትል የሚያደርግ ከሰባት ተቋማትና የተለያዩ አካላት ያሉበት ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።


በተለይም የምርት እጥረት እንዳይከሰት ከመደበኛ ገበያዎች በተጨማሪ አማራጭ የግብይት ማዕከላትን በማደራጀት አምራቹና ሸማቹ በቀጥታ የሚገናኙበት ሁኔታ በማመቻቸት ማህበረሰቡ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ መደረጉን ተናግዋል።

የክትትልና ቁጥጥር ስርዓቱም በቅንጅት እየተሰራ እና በአጠቃላይ የበዓል ገበያ የተረጋጋ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026