🔇Unmute
ኢዲስ አበባ ፤ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያን የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮጵያን ዕድገትና ልማት ሊያስቆሙ የሚሞክሩ ኃይሎችን ከማይችሉት ተራራ ጋር እየታገሉ መሆኑን በተግባር እናሳያቸዋልን ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሞጆ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፊያን መርቀው በይፋ ስራ አስጀምረዋል።
በመርሀ ግብሩ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢፌዴሪ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያን የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ባለፉት ጥቂት ወራት የተመዘገቡ በርካታ ስኬቶች ለነገዋ ኢትዮጵያ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ሚሊዮን የሚልቁ ዜጎች ድምፅ በመስጠት ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚመራቸውን መንግሥት የመረጡበት፣ ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ አራት ሺህ ዜጎች በጋራ መክረውና ዘክረው የኢትዮጵያን መፃኢ ጊዜ የወሰኑበት፣ ስምንት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል ጠቅላላ ድምሩን 56 ቢሊዮን ማድረስ የተቻለበት ዓመት መሆኑንም ተናግረዋል።
እነዚህ የስምረት የድልና የመከናወን ስኬቶች ተሰናስለው ኢትዮጵያ ከ10 ነጥብ 2 በመቶ በላይ ዕድገት እንድታስመዘግብ አስችሏታል ብለዋል።
እንደ ኢትዮጵያ ሰፊ ህዝብ ያለው ሀገር ለማደግ ሎጂስቲክስ ከፍተኛ ጉልበት እንዳለውም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።

ሎጂስቲክስ ከትራንስፖርት፣ ወደብ፣ የባቡር መሰረተ ልማት ለአርሶ አደሩ እስከሚደርስ ያለውን ሰንሰለት የያዘ መሆኑን ገልጸው፤ ለኢትዮጵያ ዕድገት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።
የሎጂስቲክስ አገልግሎት ችግር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አንቆ የቆየ መሆኑን በማንሳት፣ የሞጆ ሎጂስቲክስ ማዕከል እነዚህን ችግሮች እንደሚፈታ ገልጸዋል።
የሞጆ የሎጂስቲክስ ማዕከል የኮንቴነር የመያዝ አቅም ከ500 ሺህ ወደ አንድ ሚሊዮን ያሳድጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዕድገት የተሟላ እንዲሆን ሁሉም ማዕዘናትን ከጫፍ ጫፍ ማገናኘት እንደሚገባ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስገነዘቡት።
በ2018 ዓ.ም የብዙ ድል፣ ስኬትና መከናወን ዘመን እንደነበር ገልጸው፤ በ2019 ዓ.ም የላቀ የምንፈፅምበት ዓመት እንደሚሆን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሰላም እንደሚሻሻል ጠቁመው፤ ከጀመርነው ዕድገትና ልማት ሊያስቆሙን የሚሞክሩ ኃይሎችን ከማይችሉት ተራራ ጋር እየታገሉ መሆኑን በተግባር እናሳያቸዋለን ሲሉም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፤ኢትዮጵያን የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።
ልጆቻችን የተሻለች ሀገር እንዲረከቡ ያለብንን አደራ በሙሉ ዕምነትና ብቃት እናከናውናለን ሲሉም ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026