🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ):- ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ማስቀጠል የምትሻው የቅኝ ግዛት ፍላጎት ላይመለስ አክትሟል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ገለጹ።
ኢትዮጵያ ወንዞቿን አልምታ ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ እንደማትሻም ተናግረዋል።
አምባሳደር ዘሪሁን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በኢትዮጵያውያን ደምና ላብ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተፋሰሱ ሀገራት በውሃ ሀብታቸው ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ የልማት ፕሮጀክት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ይህም የግብፅን ወንዙን በብቸኝነት የመቆጣጠር የብቸኝነት ዘመን ማብቃቱን ማሳያ ነው ብለዋል።
በቀጣይም በዓባይና በገባር ወንዞች ላይ የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት የማይጎዱ ነገር ግን የኢትዮጵያን የመልማት መሻትና ብሔረዊ ጥቅም የሚያስጠበቁ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም በአፅንኦት ጠቅሰዋል።
በወንዞቿ ላይ የሚገነቡት የኃይል ማመንጫና የመስኖ ግድብ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የልማት ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ቀጣናዊ ትስስርንና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ግብፅ ደካማ የውሃ አስተዳደር ያላትና ውሃ አባካኝ ሀገር መሆኗን በማንሳት፥ የአስዋን ግድብ በበረሃማ አካባቢ መገንባቱ ከፍተኛ የውሃ ትነትን በማስከተል ከፍተኛ የውሃ ብክነት እንዲከሰት እያደረገ ነው ብለዋል።
በዚህም ከ14 እስከ 16 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የሚጠጋ ውሃ እንደሚባክን አንስተዋል።
በአንጻሩ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሀብትን በተቀናጀ ሙያዊ የውሃ አስተዳደር የሚመራና ያለምንም ብክነት ለኢትዮጵያና ለሌሎች የተፋሰሱ ሀገራት የልማት እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።
ግብፅ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ዘመን የውል እሳቤ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን በተፈጥሮ ሀብታቸው የመልማት መብታቸውን እንዳይጠቀሙ አስሮ ማቆየቱን ጠቅሰዋል።
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ይህ አካሄድ አይሠራም ያሉት አምባሳደር ዘሪሁን፣ የግብፅ ሰሞናዊ ለቅሶ የዓለም አቀፍ የውሃ ሕግን ካለማወቅ የመነጨና መቼም የማይመለሰውን በብቸኝነት የመጠቀም አካሄድን የማስቀጠል ከንቱ ጥረት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ዓባይ ወንዝን ለማልማት የማንንም ይሁንታ እንደማትጠይቅም አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ወንዞቿን ስታለማ የጋራ ተጠቃሚነትን፣ ፍትሐዊና ምክንያታዊ መርሆችን መሰረት በማድረግ መሆኑንም ተናግረዋል።
ግብፅ የዓባይ ወንዝ ተቀባይ ሀገር እንደመሆኗ በትብብር መስራት ብቸኛ አማራጯ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026