🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አዲስ ሪፎርም ወደ ሥራ መግባቱን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ገለጹ።
ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ ፤ ታላቅ ርዕይ
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠንካራ የሥርዓት ግንባታና ጠንካራ መንግሥትን መመሥረት የሚያስችል አዲስ ሪፎርም ወደ ሥራ ማስገባቱን ነው የክልሉ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የገለጸው።
የአገልግሎቱ ሃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ በጨፌ ኦሮሚያ ጸድቆ ወደ ሥራ የገባው አዲሱ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሪፎርም የብልፅግና ጉዞን ለማላቅ የተዘጋጀ ነው።
ይህ መዋቅር ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ የመንግሥትና የሥርዓት ግንባታን እንዲሁም የሕዝብን ተጠቃሚነት ስኬታማ የሚያደርግ መሆኑንም አክለዋል።
በዚህ ሪፎርም በክልል ደረጃ የነበሩት 58 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ወደ 41 ዝቅ እንዲሉና ተመሳሳይ ሥራ ያላቸው ተመልሰው እንዲደራጁ የተደረገ ሲሆን፣ በዞን ደረጃም የነበሩት 21 ዞኖች ወደ 6 ዞኖች መደራጀታቸውን ገልጸዋል።
የዚህ አዲስ ሪፎርም ዓላማ የውሳኔ ሰጪነት ሥልጣን እስከ ቀበሌ ደረጃ ድረስ ዝቅ እንዲል፣ በክልል ደረጃ ተወሰኖ የነበረው አገልግሎት ወደ ታች ወርዶ ሕዝቡ የሚፈልገውን አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኝ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም አቶ ሀይሉ ተናግረዋል።
አክለውም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሁሉም ዘርፍ እየተመዘገቡ ያሉ ግቦችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከ2019-2023 የሚቆይ ራሱን የቻለ የአምስት ዓመት ዕቅድ በኦሮሚያ ጨፌ ማጽደቁንም አንስተዋል።
ይህ ራሱን የቻለ ዕቅድ ከመደመር እሳቤ የተቀዳ፣ በቁርጠኝነት የሚመራ፣ ከትራንስፎርሜሽን ሽግግር ወደ መዝለል የሚደረገውን ጉዞ በማረጋገጥ የብልፅግና ጉዞን መሠረት ለማስያዝ የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል።
አቶ ሀይሉ በመጨረሻም ክልሉ ከሁለት ዓመት በፊት የመንግሥት አገልግሎትን ለህብረተሰቡ በቅርበት ለማዳረስ አዲስ የቀበሌ አደረጃጀት ማዋቀሩን በማስታወስ፣ የአሁኑ የዞኖች መዋቅርም ይህንን የቀበሌ አደረጃጀት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026