🔇Unmute
ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል።የመደመር መንግሥት ከትናንት በስትያ በይፋ በተመሠረተበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርላማ ያቀረቡት ንግግር የመንግሥቱን አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን የወደፊት ራዕይ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የንግግራቸው ማዕከላዊ ጭብጥም ኢትዮጵያ ዘላቂ ችግሮቿን የምትፈታው በራሷ የሥልጣኔ መንገድ ስትጓዝ ብቻ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የብዝሃ ሥልጣኔ ሀገር መሆኗን አንስተዋል። ለዘመናት የታሪክ፣ የባህል፣ የእምነት እና የማንነት መገናኛ ሆና ቆይታለች። ለብዙ ሕዝቦች መነሻ፣ ለብዙ ትውልዶች መነቃቃት ምንጭ የሆኑ ታሪኮችን በውስጧ ይዛለች። ሆኖም ይህን ታላቅ ቅርስ ወደ ዘላቂ ልማትና ዕድገት በመቀየር ረገድ ፈተናዎች በተደጋጋሚ ያጋጥማሉ።
የጀመርነውን ማስቀጠል፣ የተገነባውን ማስጠበቅ እና በትውልድ መካከል ቀጣይነትን ማረጋገጥ ትልቁ ፈተና መሆኑንም አስገንዝበዋል።አንድ ትውልድ የገነባውን ሌላው ትውልድ እያፈረሰ የሚሄድበት ሁኔታ ሥልጣኔን እንደማይፈጥር ፣ ሀገርንም እንደማያበለጽግ አብራርተዋል።
በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ በብዙ ዘርፎች ያላትን አቅም ሙሉ በሙሉ መጠቀም አልቻለችም። ሀሳብን በውይይት ከመፍታት ይልቅ በኃይል ለማስፈጸም የተደረጉ ጥረቶች ሀገሪቱን ወደ ኋላ ጎትተዋል።
በመሆኑም የመደመር መንግሥት መልዕክት ግልጽ ነው፤ የኢትዮጵያ ችግሮች መፍትሔ የሚገኘው በግጭት ሳይሆን በመግባባት፣ በመደመር እና በጋራ ግብ ዙሪያ በመሰባሰብ ነው።
አዲሱ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማለት የመከባበር ባህልን መገንባት፣ ሕግን ማክበር፣ ልዩነቶችን እንደ ጥንካሬ መቀበል እና የጋራ ሀገራዊ ራዕይ መፍጠር ነው። ይህ ደግሞ ስሜትን በማሸነፍ፣ ጥላቻን በመተው እና አቅምን በጋራ በማሰባሰብ የሚሳካ ታላቅ ሀገራዊ ርዕይ ነው።
በዚህ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር የመንግሥት ቀዳሚው አጀንዳው ነው። ከሁሉም የዓለም ሀገራት ጋር የሚደረገው ግንኙነት የኢትዮጵያን ጥቅም እና ተጽዕኖ የሚያሳድግ መሆን አለበት ብለዋል። ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያ በሌሎች ፍላጎት የምትመራ ሳይሆን በራሷ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ተመስርታ የምትወስን ጠንካራ ሀገር መሆኗን ነው።
በቀጣናውም ኢትዮጵያ የመረጋጋት እና የትብብር ማዕከል ሆና ትቀጥላለች። ጎረቤቶቿ በተፈጥሮ ያገኘቻቸው አጋሮቿ በመሆናቸው የጋራ ጥቅም፣ የሰላም እና የትብብር መርሆዎች የውጭ ግንኙነቷ መሠረት እንደሚቀጥሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም በማስከበር እና በጋራ ጥቅም መርህ ላይ ተመስርታ የቀጣናው ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር ለመሆን ትሰራለች።
በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምሥረታ የአስተሳሰብ ለውጥ፣ የሥልጣኔ ግንባታ ጥሪ እና ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ አዲስ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ ነው። ይህ ጉዞ ስኬታማ የሚሆነው ደግሞ መንግሥት፣ ፓርላማ፣ ተቋማት እና ሕዝብ በአንድ ራዕይ ሲተባበሩ ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ ያላትን ታሪካዊ ቅርስ ወደ ዘመናዊ ሥልጣኔ በመቀየር፣ ብሔራዊ ጥቅሟን በማስከበር እና በቀጣናው የሰላም አርበኛ ሆና በመቆም አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅታለች።
የኢትዮጵያ ዘላቂ ብልጽግና፣ የሕዝቦቿ አንድነት እና የቀጣናው ደህንነት የሚረጋገጠው አዲስ ኢትዮጵያዊ ሥልጣኔ በሚገነባበት መጠን ነው።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026