🔇Unmute
ጅማ፣ መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፡- የጅማ ከተማ ነዋሪዎች አዲስ የተመሰረተው መንግስት በልማት፣ በዲፕሎማሲና በባህር በር ጉዳይ ላይ የጀመራቸውን ስራዎች እንዲያጠናክር ጠየቁ።
7ኛ የህዝብ ተውካዮች ምክር ቤት አንደኛ አመት የስራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መሰየሙ ይታወቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግርም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲና በሌሎች መስኮች በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኢዜአ ያነጋገራቸው የጅማ ከተማ ነዋሪዎች መንግስት በልማት፣ በኢኮኖሚ መረጋጋትና በዲፕሎማሲ ዘርፍ የጀመራቸው ተስፋ ሰጭ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ጠቁመዋል።
አስተያየታቸውን ከሰጡ የከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ ሳሊ አለሙ አዲስ የተመሰረተው መንግስት የባሕር በርን ለማሳካት የጀመረውን ጉዳይ እውን ለማድረግ የበለጠ ሊተጋ እንደሚገባ አመልክተዋል።
ጉዳዩ የኢትዮጵያውያን የህልውና ጥያቄ በመሆኑ መንግስት በዘርፉ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመልክተዋል።
ዜጎችም አንድነታቸውን ጠብቀው ለሀገራዊ ጉዳዮች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ይበልጥ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የከተማው ነዋሪ አቶ ነዚፍ ተማም አዲስ የተመሰረተው መንግስት የባሕር በርን ለማሳካት የመንግሥትና ሕዝብ አቅምን በማቀናጀት ሁሉም የዜግነት ግዴታውን የሚወጣበትን አውድ ማስፋት እንደሚገባውአመልክተዋል።
የመደመር መንግሥት መመስረቱ በከተማና በገጠር የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር ትልቅ ተስፋ እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
መንግሥት በቀጣይ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚያደርገው ሥራ በዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንዳለበትም አክለዋል።
ወጣት ቦና ሮቢ በበኩሉ አዲስ የተመሰረተው መንግሥት የልማትና የመልካም አስተዳደር ማነቆዎችን በመፍታት ለስራ እድል ፈጠራና ለወጣቶች ኢኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

የወጣቶችን የልማትና የፖለቲካ ተሳትፎ ለማጠናከር የተቀየሰውን እቅድ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ለመወጣት መዘጋጀቱን ጠቁሟል።
አቶ ሙልዬለት ታደሰ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲውና በሌሎች ዘርፎች ያላትን ዓለም አቀፋዊ ቁመና ማስቀጠል እንደሚገባት አስገንዝበዋል።

ለዚህም ኢኮኖሚያዊ ሉአላዊነትን ለማጽናት የተጀመሩ እንደ ኮሪደር ልማትና የኢንዱስትሪ ልማቶች በቀጣይ በከፍተኛ ደረጃ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026