🔇Unmute
ጎንደር ፣መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በተያዘው የበጋ ወቅት ከ734 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ በዘንድሮ የበጋ ወቅት የመገጭ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ የውሀ አማራጮችን በመጠቀም የመስኖ ልማት ይካሄዳል።

በመስኖ ልማቱ ጥቅም ላይ የሚውሉ ስምንት ሺህ የሚደርሱ የውሃ መሳቢያ ሞተሮች ለአርሶ አደሩ እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል።
በግንባታ ላይ የሚገኙ ከ80 በላይ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ልማቱ ለማስገበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይም የመገጭ ግድብ በክረምት ወቅት በቂ ውሀ በመያዙ ለመስኖ ልማቱ ተደማሪ አቅም እንደሚፈጥር አመልክተዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መስፍን አበጀ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለጹት በክልሉ በዘንድሮው በጋ ከ734 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ነው።
ከዚህ ወስጥም 400 ሺህ ሄክታር የሚሆነው መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ በማልማት ከቤት ፍጆታ አልፎ ለኢንዱስትሪ ግብአትና ለገበያ የሚውል መሆኑን አመልክተዋል።
በቀሪው መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ስራስርና ሌሎች እንደ በቆሎ ያሉ ሰብሎች እንደሚለሙ ጠቅሰዋል።
በበጋ መስኖ ልማቱ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ከዚህ ቀደም ወደ ልማት ያልገባ 250 ሺህ ሄክታር መሬት ወደ ልማት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዙ የማዳበሪያና ምርጥ ዘር አቅርቦትና ስርጭት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል ።
በአማራ ክልል ከሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት የሚያስችል አቅም መኖሩን የቢሮው መረጃ ያመላክታል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026