የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ ለሕዝብ ተጨባጭ ውጤት የሚያስመዘግቡ የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

Oct 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ ለሕዝብ ተጨባጭ ውጤት የሚያስመዘግቡ የልማት ሥራዎችን በትብብር ለማስቀጠል እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባዎች ዛሬ በታይላንድ ባንኮክ ዛሬ ተጀምሯል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባዎች ላይ ለመሳተፍ ባንኮክ ይገኛል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ትዕግስት ፍስሃ በልዑካን ቡድኑ ተካተዋል።

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከዋናው ስብሰባ ጎን ለጎን ከዓለም ባንክ ምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ምክትል ፕሬዚዳንት ንዲያሜ ዲዮፕ (ዶ/ር) ጋር በሁለገብ የልማት ትብብሮች ላይ ምክክር አድርጓል።

ውይይቱ በኢትዮጵያና በዓለም ባንክ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ጠንካራ አጋርነት ለመገምገም፣ የወደፊት የትብብር አቅጣጫዎችና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች ለመወሰን ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ውይይት ከተደረገባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አዲሱ ሀገር አቀፍ የትብብር ማዕቀፍ (Country Partnership Framework) ይገኝበታል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ዘላቂነትን ማረጋገጥ፣ ተወዳዳሪ የግል ዘርፍ እንዲኖር ማድረግና የወጪ ንግድን ማሳደግ፣ ዘመናዊና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተጣጣመ የግብርና እሴት ሰንሰለት መገንባት፣ ዘላቂ የመሠረተ ልማት ዝርጋታንና ቀጣናዊ የኃይል ትስስርን ማስፋፋት እንዲሁም የሰው ሀብት ልማትና የማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓቶችን ማጠናከር በቀጣይነት ትኩረት የሚሰጣቸው አጀንዳዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

በተጨማሪም ልዑኩ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 ለምታዘጋጀው 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ከዓለም ባንክ የሚደረገው የቴክኒክ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና በሥራ ላይ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንዲፋጠን ጥሪ አቅርቧል።

ሁለቱም ወገኖች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተጨባጭና ዘላቂ ውጤት ለማስመዝገብ በትብብርና በቁርጠኝነት ለመሥራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026