🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን የልማት ስትራቴጂዋ ማዕከል በማድረግ እየሰራች እንደምትገኝ የገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታ ትዕግስት ፍስሃ ገለጹ።
የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብስባ በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ ነው።
ከዓመታዊው ስብስባው ጎን ለጎን የሰው ሰራሽ አስተውሎት የተመለከተ ውይይት ተደርጓል።
በውይየቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታ ትዕግስት ፍስሃ ተሳትፈዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የዓለም ባንክ፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የጌትስ ፋውንዴሽን አመራሮች ተገኝተዋል።
የምክክር መድረኩ በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለአካታች ኢኮኖሚያዊ እድገትና ለዘላቂ ልማት መጠቀም ላይ የጋራ እይታዎችን ለመለዋወጥ እና ተጨባጭ የትብብር መስኮችን ለመለየት የሚያስችል እድል ፈጥሯል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታ ትዕግስት ፍስሃ፣ ኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በልማት ስትራቴጂዋ የቅድሚያ ትኩረት በመስጠት እየሰራች እንደምትገኝ አመልክተዋል።
እ.አ.አ በ2019 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩትን እና በግንባታ ላይ የሚገኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ የዚሁ ስራ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ሚኒስቴር ዲኤታዋ የአፍሪካን ነባራዊ ፈተናዎች፣ መረጃዎችን እና የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን መሰረት ያደረጉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መፍትሄዎችን የማላመድ፣ የመተግበር እና በሂደትም የማልማት አቅምን በመገንባት አህጉሪቷ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የእሴት ሰንሰለት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳለባት አስምረውበታል።
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በቀጣናዊ ትስስር እና በህጋዊ ማዕቀፎች ዙሪያ ከልማት አጋሮች ጋር በትብብር ለመስራት ያላትን ሙሉ ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ የዓለም ባንክ እና ሌሎች የልማት አጋሮች የኢትዮጵያን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት እና ዩኒቨርሲቲ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መደረጉን የ...
Oct 16, 2026
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026