🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ጥቅምት 6/2019(ኢዜአ)፦የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና በዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን፣ ከአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ዮዜፍ ሲኬላ (Jozef Síkela) ጋር ተወያይቷል።
በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ የልማት አጀንዳዎችና በቀጣይ ትብብሮች ዙሪያ መክረዋል።
የአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ዮዜፍ ሲኬላ (Jozef Síkela) በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አስተማማኝ አጋር መሆኗን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ እና በተለይም ለቀይ ባህር ቀጣና ሰላምና መረጋጋት የምታበረክተውን የላቀ አስተዋፅዎ እና በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ ቁልፍ ሚና አድንቀዋል።
አክለውም የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መደረጉን የ...
Oct 16, 2026
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026