የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በአፋር ክልል የጥጥ ምርታማነትንና ጥራትን ለማሳደግ እየተከናወነ ያለው ተግባር ውጤት ተገኝቶበታል

Oct 22, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሰመራ ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ) ፦ በአፋር ክልል የጥጥ ዘር አቅርቦትን በራሰ አቅም በመሸፈን ምርታማነቱንና ጥራቱን ለማሳደግ እየተከናወነ ያለው ተግባር ውጤት ታይቶበታል ሲሉ በአፋር ክልል በጥጥ ልማት ስራ ላይ የተሰማሩ አልሚዎች ገለፁ።

«ጥጥን እናልማ፤ ሀብትን እናፍራ፣ ብልፅግናን እናረጋግጥ» በሚል መሪ ሐሳብ ዓለም አቀፍ የጥጥ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ ለአራተኛ ጊዜ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በመስክ ምልከታ ተከብሯል።


በአፋር ክልል በጥጥ ልማት የተሰማሩ አልሚዎች እንዳሉት፤ በክልሉ የጥጥ ዘር አቅርቦትን በራሰ አቅም በመሸፈን ምርታማነቱንና ጥራቱን ለማሳደግ እየተከናወነ ያለው ተግባር ውጤት ታይቶበታል።


ከመተማ የመጡት አቶ ሃብቱ ፅዱ እንደገለጹት፤ የዝናብ እጥረት የሚስተዋልበት የአፋር ክልል በመስኖ እየተከናወነ ያለው የጥጥ ልማት የሚደነቅ ነው።

በተለይም የጥጥ ዘርን በውጭ ምንዛሬ ገዝቶ ወደ አገር ውስጥ ከማስገባት ይልቅ በራስ አቅም ተኪ ምርትን በማምረት ለመሸፈን እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።


ከሁመራ የመጡት ጥጥ አምራች ጣሰው ማሞ በበኩላቸው፤ ዘርን በራሳቸው አቅም በመሸፈን የጥጥ ሰብል በዝናብ ከሚለማው ይልቅ በአፋር ክልል በመስኖ እየለማ ያለው ጥጥ የተሻለ ልምድ እንደወሰዱበት ተናግረዋል።


የሲምብሌታ አጠቃላይ እርሻ ልማት ባለቤት የሆኑት አቶ መሐመድ ኡዳ፤ በ1 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ አምስት ዓይነት የጥጥ ዘሮችን በማላመድ ላይ መሆናቸውን ገልጸው ይህም በዘርፉ ለሚደረገው የምርምር ሥራ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።


በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን ሃሩካ ወረዳ በ200 ሄክታር መሬት ላይ ጥጥ በማልማት ላይ የሚገኙት አሚና ኢሴ በበኩላቸው፤ የጥጥ ዘር አቅርቦት በባለቤትነት መሠራቱ በክልሉ በመካሄድ ላይ ካለው የጥጥ ልማት የተሻለ ምርት ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።


የጥጥ ምርታማነትን ለማሳደግ ከዘር አቅርቦት በተጨማሪ ፀረ አረምና ፀረ ተባይን ለመጠቀም በምርምር የተደገፈ ሥራ እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በግብርና ሚኒስቴር የጥጥ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሳምሶን አሰፋ ናቸው።

ክልሎችም በየአካባቢያቸው ያለውን ፀጋ ለይተው እንዲያለሙ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጓል- አፈ ጉባዔ አሕመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መደረጉን የ...

Oct 16, 2026

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026