🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ የመደመር መንግሥት ለአምራች ኢንዱስትሪው በሰጠው ልዩ ትኩረት ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።
የመደመር መንግሥት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን መዛባት በዘላቂነት ለማስተካከል መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ አካሄዷል።
የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በተለይ በአምራች ዘርፉ የነበሩ ማነቆዎችን በመፍታት ተኪ ምርትና የወጪ ንግድ እንዲያድግ እያስቻለ ይገኛል።
የሀገር ውስጥ አምራቾች በገበያ ላይ ያላቸው የምርት ድርሻ ወደ 45 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ የፋብሪካዎች አማካይ የማምረት አቅምም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ ከ69 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በመደመር መንግሥት ኢንዱስትሪ የኢትዮጵያ የወደፊት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር እንዲሆን አበክሮ እየሰራ ነው።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ሀገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ካደጉ ሀገራት መካከል የሚጠቀሱ በመሆኑ ይህንን ተሞክሮ በመውሰድ በዘርፉ ላይ ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ነው ያነሱት።
የመደመር መንግሥት በዘርፉ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር በመፍጠር፣ ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያን በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የአፍሪካ ማዕከል በማድረግ የቆዳ፣ ጨርቃጨርቅ፣ የምግብ እና መጠጥ፣ የግንባታና ሌሎች ግብአቶችን በብዛት ወደ ውጭ ለመላክ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል።
የማምረቻው ዘርፍ እድገት በ2013 ዓ.ም 4 ነጥብ 8 ከነበረው በ2018 ዓ.ም 15 ነጥብ 8 በመቶ መድረሱን አንስተው ይህንን እድገት በዘላቂነት ለማስቀጠል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
ለማምረቻው ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት አምራቾች የሚያጋጥማቸውን ማነቆዎች በመፍታትና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
የመሬት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የግብዓት፣ የብድር እንዲሁም ሌሎች አቅርቦቶች ላይ ከፍተኛ መሻሻሎች መታየታቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪው የገበያ ድርሻም ከ30 በመቶ ወደ 46 ነጥብ 4 በመቶ ማደጉን ገልጸው፤ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩንም ተናግረዋል።
እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፤ ከገቢ እና ወጪ ምርት ወደ 32 በመቶ የሚሆነው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ስራዎች በመሆኑ ይህንን ለመቀነስ እየተሰራ ነው።
በአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ ቀልጣፋ አገልግሎቶችን በመስጠት ጊዜና ወጪን የመቀነስ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ኢንቨስትመንት ላይ ምቹ ከባቢ ሁኔታ በመፍጠር እንዲሁም ማበረታቻዎች ተግባራዊ በመደረጋቸው በዘርፉ የተሰማሩ የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንቶች ቁጥር መጨመሩን ጠቅሰዋል።
የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትስስርንም በማጠናከር የሰለጠነ የሰው ሀይል በማፍራት፣ የማምረቻ ዋጋን በመቀነስ እንዲሁም ምርታማነትን በማሻሻል የአገሪቱ ተወዳዳሪነት እያደገ ይገኛል ብለዋል።
በሌላ በኩል በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 24 ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል 20ዎቹ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን መቀየራቸውን አንስተዋል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ በስራ እድል ፈጠራ፣ የተኪ ምርትና ወደ ውጭ መላክ፣ የገበያ ትስስር፣ የምርት ጥራትና ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጦች መገኘታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መደረጉን የ...
Oct 16, 2026
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026