🔇Unmute
አሶሳ፤ ጥቅምት 20/2019 (ኢዜአ)፦ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ሶስት ወራት 3 ሺህ 833 ኪሎግራም ወርቅ ወደ ብሄራዊ ባንክ መግባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አስር ኢብራሂም ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በበጀት ዓመቱ 12 ሺህ 928 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት ዕቅድ ተይዞ ወደ ስራ ተገብቷል።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከባህላዊ እና ልዩ አነስተኛ የወርቅ አምራቾች 3 ሺህ 833 ኪሎግራም ወርቅ ወደ ብሄራዊ ባንክ መግባቱን ገልጸዋል።
አፈጻጸሙ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ መጨመሩን ገልፀው ለዚህም ፈቃድ የወሰዱ ተጨማሪ አምራቾችን ወደ ስራ ማስገባት በመቻሉ እና ግብይቱ ላይ የክትትል እና ቁጥጥር ስራ በመሠራቱ ነው ብለዋል።
በክልሉ የማዕድን ዘርፍ ለበርካታ ዜጎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የኢኮኖሚ ምንጭ መሆኑን ጠቁመው ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ እና የስራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በበጀቱ ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራትም በክልሉ ከ5 ሺህ 300 በላይ ዜጎች በዘርፉ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ከማዕድን ፈቃድና ከተለያዩ አገልግሎቶች ቢሮው በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ36 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ኃላፊው አስታውቀዋል።
በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ሀብቶችን በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማስቀጠል በህግና ስርዓት እንዲመራ መደረጉን አስረድተዋል፡፡
የሚያጋጥሙ ችግሮችንም በየጊዜው በመገምገም እና መፍትሔ በመስጠት በማዕድን ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቀነስ ቀጣይነት ያላቸው ስራዎች እንደሚሰሩ አመላክተዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መደረጉን የ...
Oct 16, 2026
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026