🔇Unmute
ሆለታ፣ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፡- የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በአፈር አጠቃቀምና እንክብካቤ ላይ የተለያዩ ምርምሮችን እያካሄደ መሆኑን ገለጸ።
በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል የአፈር ለምነት ተመራማሪ አቶ ዘለቀ ኦብሳ እንዳሉት፤ ሆለታ ግብርና ምርምር በኮትቻ አፈር ምርምር ላይ የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ነው።
በዚህም ኮትቻ አፈር በዝናብ ጊዜ ውሃን በብዛት መያዝ እና በበጋ ወቅት በስፋት መሰነጣጠቅ ዋነኛ ችግር መሆኑን በመለየት እንደ አፈር ማጠንፈፍ የመሳሰሉ መፍትሔዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር አሳሳቢ የሆነው የአፈር መሸርሸርን ለመታደግ በአፈር አጠቃቀምና እንክብካቤ ዙሪያ ሰፋፊ የጥናት ስራዎችን በማካሄድ ላይ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም ከህዝብ ቁጥር መጨመርና ከአጠቃቀም ጉድለት የተነሳ ከፍተኛ የአፈር መሸርሸር ስለሚኖር ለዚህ መፍትሔ የሚሆኑ ውጤቶችን ለማምጣት ተግቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በአፈርና ውሃ ምርምር ስር ስድስት የትኩረት መስኮች አሉት። እነዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ በማዕከሉ አስተባባሪነት የሚካሄደው የአፈር አሲዳማንት ምርምር፣ በአፈር ለምነት ላይ የሚካሄድ ምርምር፣ የተፋሰስ ልማት፣ የኮትቻ አፈር ጥናት እና የተፈጥሮና ማዳበሪያ ዝግጅት ላይ የሚካሄዱ ምርምሮችን እንደ አብነት አንስተዋል።
ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ የአፈር፣ የእፅዋትና የውሃ ምርምር ላቦራቶሪዎች እንዳሉት አንስተው በዚህም የምርምር ውጤቶቹን ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለአርሶ አደሮች በመስጠት ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ለአብነትም ቀደም ሲል በውል የማይታወቀው የአፈር አሲዳማነት ችግር በአሁኑ ጊዜ ችግሩ በምርምር ተለይቶ አፈሩን በማከምና የእርሻ ስራውን በማስተካከል ምርትና ምርታማነት መጨመር መቻሉን እንደ ምርምር ውጤታቸው አንስተዋል።
አፈርን በኖራ ከማከም ባለፈ አሲዳማ አፈር ተቋቁመው የተሻለ ምርት መስጠት የሚችሉ የሰብል ዝርያዎችም በምርምር ተገኝተው ለአርሶ አደሮች በመስጠት ውጤት ማስገኘታቸውን አንስተዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 /2019 (ኢዜአ)፦የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አርሶና አርብቶ አደሩ በአነስተኛ የመሬት ይዞታ ላይ ብዝኅ የግብርና ምርቶችን በማምረት...
Nov 5, 2026
ጎንደር፣ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ):- የመገጭ ግድብ ግንባታ ከመስኖ ልማት ባለፈ ለዓሳ ሃብት ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለጸ። የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀ...
Nov 4, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መደረጉን የ...
Oct 16, 2026
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026