🔇Unmute
አሶሳ፤ ህዳር 2/2019(ኢዜአ)፦በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ምቹ የሥራና የመኖሪያ ከባቢን ፈጥሯል ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
በአሶሳ ከተማ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በርካታ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጨምሮ ምቹ የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገዶች ተገንብተዋል።
ነዋሪዎቹ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተገነባው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበት ከማጉላት ባለፈ ለነዋሪዎቿ ምቹ የሥራ ከባቢን ፈጥሯል።

በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች የተጀመረው የኮሪደር ልማት በአሁኑ ወቅት ሁሉንም አካባቢዎች ተደራሽ እያደረገ ይገኛል ሲሉም ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል።
ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ አህመድ አበይም እንደተናገሩት፣ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ገጽታ የቀየረና ለነዋሪዎቿ ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢ የፈጠረ ሆኗል።
በተለይም በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ መንገዶች የተከናወነው የኮሪደር ልማት ከዚህ ቀደም የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያገኙ አካባቢዎች በኤሌክትሪክ ኃይል ገፅታቸው እንዲቀየር ተደርጓል ብለዋል።

የኮሪደር ልማት የሚያስገኘውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በመረዳት ሕብረተሰቡ የልማቱ ተባባሪ መሆን እንዳለበትም አመልክተዋል።
ሌላው የከተማዋ ነዋሪ እስማኤል ረመዳን በበኩላቸው፣ በሰፈራቸው የተገነባው የኮሪደር ልማት በመብራት ያሸበረቀ በመሆኑ ከዚህ ቀደም በምሽት ለመንቀሳቀስ አስፈሪ የነበረውን ጊዜ እንዳስቀረው ገልጸዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር እንደገለጹት፣ በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በጥራትና በፍጥነት እንዲሁም የተሟላ መሠረተ ልማትን ያካተተ ነው።
በአሶሳ ከተማ በሁሉም አካባቢዎች የኮሪደር ልማትን በማከናወን ከተማዋን ይበልጥ ውብና ጽዱ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ እንደሚቀጥል ጠቁመው፣ በከተማዋ ውስጥ የወንዝ ዳርቻ ልማት ለማከናወን ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ከኮሪደር ልማቱ ጎን ለጎንም ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በሆቴል ግንባታ ዘርፍ ባለሃብቶች ትልልቅ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የአሶሳ ከተማን ጨምሮ በግልገል በለስ፣ በባምበሲ እና በካማሽ ከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች በጥራት እንዲከናወኑ ቢሮው አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 /2019 (ኢዜአ)፦የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አርሶና አርብቶ አደሩ በአነስተኛ የመሬት ይዞታ ላይ ብዝኅ የግብርና ምርቶችን በማምረት...
Nov 5, 2026
ጎንደር፣ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ):- የመገጭ ግድብ ግንባታ ከመስኖ ልማት ባለፈ ለዓሳ ሃብት ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለጸ። የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀ...
Nov 4, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መደረጉን የ...
Oct 16, 2026
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026