🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ለኢንተርፕርነርሺፕ ምቹ ሥነ-ምህዳር መፈጠሩን የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ዳይሬክተር መፍትሄ ታደሰ ገለጹ።
አለም አቀፍ ኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት እና የኢትዮጵያ ቬንቸር ጉባኤ መክፈቻ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል፡፡

የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ዳይሬክተር መፍትሄ ታደሰ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ አዳዲስ ሃሳቦችንና ፈጠራዎችን እውን ለማድረግ የሚያስችል ጠንካራ ሥነ-ምህዳር እየተገነባ ነው፡፡
ማህበረሰቡ ስራ ፈጠራን እንደ አንድ ጊዜያዊ ሁነት ወይም ክስተት ከማየት ወደ ተጨባጭ ነገር ማሸጋገር እንደሚገባ ተናግረዋል።
ስራ ፈጣሪዎች ከጥሩ ሃሳብ ባለፈ ፋይናንስ፣ ገበያ፣ ክህሎት፣ ትስስር ፣ ቴክኖሎጂ፣ አመራር እና አመቺ የፖሊሲ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልጋቸው አስገንዝበዋል።
ለዚህም ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እስከ 2030 ድረስ በአፍሪካ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ወጣቶች ሥራ እንዲያገኙ ለማስቻል እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ዘላቂ ለውጥን ማምጣት የሚቻለው በተጠናጥል ጥረት ብቻ ሳይሆን ከመንግስት፣ ከፋይናንስ ተቋማት፣ ከግል ሴክተሩ እና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በሚደረግ ጠንካራ አጋርነት እና ቅንጅት መሆኑን ተናግረዋል።
ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ ወጣቶች እና አጋር አካላት በመቆም የተሻለ ሥነ-ምህዳር ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የኮሙኒኬሽንና አጋርነት ዳይሬክተር እመቤት ተጫኔ በበኩላቸው፤ በመድረኩ በርካታ አለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ገልፀዋል።
ይሄም ለስታርትአፖች እና ለተለያዩ ቢዝነሶች አብረው ለመሥራት ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።
በመድረኩ የፈጠራ ሥራውን ይዞ የቀረበው በላይ አደፍርስ መንግስት ለስታርትአፕች የተሻለ ሁኔታዎችን እያመቻቸ እንደሚገኝ ገልፆ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ድጋፎች ለማግኘት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ተናግሯል።

ሌላኛዋ ምርቶቿን ይዛ የቀረበችው ሰለማዊት ተዘራ በበኩሏ መድረኩ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር ዜጎች እና ከምርት ፈላጊዎች ጋር ለመገናኘት፣ ልምድ ለመለዋወጥ እንዲሁም የንግድ ትስስር ለመፍጠር ጠቀሜታ እንዳለው ገልፃለች።

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 /2019 (ኢዜአ)፦የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አርሶና አርብቶ አደሩ በአነስተኛ የመሬት ይዞታ ላይ ብዝኅ የግብርና ምርቶችን በማምረት...
Nov 5, 2026
ጎንደር፣ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ):- የመገጭ ግድብ ግንባታ ከመስኖ ልማት ባለፈ ለዓሳ ሃብት ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለጸ። የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀ...
Nov 4, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መደረጉን የ...
Oct 16, 2026
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026