🔇Unmute
ጂንካ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ) ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ምርታማና በሽታን የሚቋቋሙ አስር የእንሰት ዝርያዎችን በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ እያላመደ መሆኑን ገለጸ።
በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን እና የእፅዋት ተመራማሪ ግርማ ዳዊት ለኢዜአ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ አካባቢዎች ያሰባሰባቸውን ምርታማና በሽታን መቋቋም የሚችሉ አስር የእንሰት ዝርያዎችን እያላመደ ነው።
የምርምር ማዕከሉ እያለማዳቸው ያሉ የእንሰት ዝርያዎችበአነስተኛ ቦታ በእጥፍ ምርት መስጠት የሚችሉ እንዲሁም ድርቅና በሽታን የሚቋቋሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የእንሰት ተክል በውስጡ ውሃን አከማችቶ የመያዝ አቅም ስላለው ድርቅ ቢከሰት አስቸጋሪ ጊዜውን ማለፍ እንደሚችል ጨምረው ገልጸዋል።
የእንሰት ስሩና አንጓው ለምግብነት የሚውል በመሆኑ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አንስተው ተረፈ ምርቱም ለእንስሳት መኖነት እና ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚሆን ቃጫን ማምረት እንደሚቻል ጠቁመዋል።
እስካሁን በተደረገው ሙከራ ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ውጤታማ የሆኑ የእንሰት ዝርያዎችን ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል ።


አርሶ አደሮች ቃጫና ሌሎች የእንሰት ተረፈ ምርቶችን በማምረት በጥራትና በስፋት ለኢንዱስትሪዎች በማቅረብ የተሻለ ጥቅም እንዲያገኙም ዩኒቨርሲቲው በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው የእንሰት ዝርያ እያላመደ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች መካከል በአሪ ዞን የሰሜን አሪ ወረዳ አንዱ ነው።
የወረዳው ነዋሪ አቶ ማርቆስ ተካ እና አርቲ ጠቃይ ለኢዜአ እንደገለፁት እንሰት በአካባቢው ተመራጭ ምግብ መሆኑን ጠቁመዋል ።
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከወረዳው የግብርና ባለሙያዎች ጋር በእንሰት ዙሪያ ግንዛቤ እየፈጠሩላቸው መሆኑን ጠቁመው በምርምር ማዕከላት በሚሰሩ የምርምር ስራዎች ልምድ በመቅሰም በማሳቸው በተሻለ ሁኔታ እንሰት እያለሙ መሆኑን ገልጸዋል ።
ተክሉን በስፋት በማልማት ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን ማቀዳቸውንም አመላክተዋል ።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 /2019 (ኢዜአ)፦የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አርሶና አርብቶ አደሩ በአነስተኛ የመሬት ይዞታ ላይ ብዝኅ የግብርና ምርቶችን በማምረት...
Nov 5, 2026
ጎንደር፣ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ):- የመገጭ ግድብ ግንባታ ከመስኖ ልማት ባለፈ ለዓሳ ሃብት ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለጸ። የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀ...
Nov 4, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአደረጃጀት መዋቅር በማዘመን የሕዝብ ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መደረጉን የ...
Oct 16, 2026
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026