የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በሐረሪ ክልል ወጣቶችና ሴቶች በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በመሳተፍ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው

Nov 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሐረር፤ ህዳር 16/2019 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል ወጣቶችና ሴቶች በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በመሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡

በመደመር መንግሥት እሳቤ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የአርሶ አደሩንና የከተማ ነዋሪውን ገቢ ለማሳደግ እንዲሁም የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ለማሻሻል ትልቅ አቅም እየሆነ ይገኛል።

መርሐ ግብሩ በዋናነት በእንስሳት ሀብት ልማት በተለይ በወተት፣ በዶሮ፣ በንብ እና በዓሳ እርባታ ላይ በማተኮር እየተካሄደ ሲሆን ምርታማነትን በመጨመር፣ የአመጋገብ ስርአትና ጤናን በማሻሻል ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል።

እንዲሁም ለወጣቶችና ለሴቶች የገቢ ምንጭ በመፍጠር እና የቤተሰብ ኢኮኖሚን በመደገፍ አይነተኛ ሚና በመጫወት ላይ ነው።


መርሀ ግብሩ በሐረሪ ክልልም ግብርናን በማዘመንና ቴክኖሎጂን በማሻገር የአርሶ አደሩን፣ የወጣቶችንና የሴቶችን ተጠቃሚነት እያጎለበተ ይገኛል።

የሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዳይሬክተር ናኦል አብዱማሊክ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የሌማት ትሩፋት ዋናው ግቡ በምግብ ራስን መቻልና የምግብ ሉዑዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው።

በዚህም ባለፉት ዓመታት በክልሉ በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በእንስሳትና በእንስሳት ተዋጽኦ ላይ በርካታ ስራዎች በማከናወን የዘርፉን ምርታማነት ማጎልበት ተችሏል ብለዋል።

ባለፉት አራት አመታትም ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በመርሀ ግብሩ የስራ እድል የተፈጠረላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።


ዘንድሮም ተጨማሪ ሼዶችን በሶስቱም ገጠር ወረዳዎች በመገንባትና ዶሮን ጨምሮ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው ላሞችን በማቅረብ ወጣቶችና ሴቶችን በእንቁላልና በወተት ሃብት ልማት ላይ እንዲሰማሩ መደረጉን ተናግረዋል።

በበጀት አመቱ ሦስት ወራትም ለ365 ወጣቶችና ሴቶች በዘርፉ የስራ እድል መፈጠሩን ጠቅሰዋል።

በዚህም ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ ለከተማው ማህበረሰብ ለማቅረብ የበለጠ አቅም እየተፈጠረ መምጣቱን አመልክተዋል።


በዚህ አመት የስራ እድል ከተፈጠረላቸው መካከል የሶፊ ወረዳ ነዋሪ ወጣት ኦብሳ ይሱፍ እና ወጣት አዚዛ መሀመድ በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በዶሮ እርባታ ዘርፍ መሰማራታቸውን ተናግረዋል።

በዘርፉ በተደረገላቸው ድጋፍ በመታገዝ ውጤታማ ለመሆን እየተጉ መሆኑን ገልጸዋል።


ወጣት ናስር ጀማል በበኩሉ በተደረገለት የመስሪያ ቦታ ድጋፍ በመታገዝ በከብት እርባታ ስራ መሰማራቱን ገልጿል።

ወተትና የወተት ተዋጽኦ በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚ እየቀረበ መሆኑን ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት ያጠናክራል -ምሁራን

አሶሳ፤ ህዳር 16/2019(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ለቀጣናው ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስርና የጋራ ተጠቃሚነት ጉልህ አስተዋጽ...

Nov 26, 2026

በሐረሪ ክልል ወጣቶችና ሴቶች በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በመሳተፍ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው

ሐረር፤ ህዳር 16/2019 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል ወጣቶችና ሴቶች በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በመሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢ...

Nov 26, 2026

ኢትዮጵያና ዩጋንዳ ለአፍሪካ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትና ለጋራ ዕድገት ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ያጠናክራሉ- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 15 /2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ዩጋንዳ ለአፍሪካ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትና ለጋራ ዕድገት ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር እንደሚያጠናክሩ ምክ...

Nov 25, 2026

በማህበር በመደራጀት በሌማት ትሩፋት የንብ ማነብ ስራ በመሰማራት የተሻለ ገቢ ማግኘት ችለናል -አርሶ አደሮች

ቦንጋ ፣ ህዳር 12 /2019 (ኢዜአ)፦ በካፋ ዞን ሺሾ-እንዴ ወረዳ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብሩ የንብ ማነብ ሥራ ላይ በመሰማራት የተሻለ ተጠቃሚ መሆናቸውን አ...

Nov 23, 2026