የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ምርት ስሌት መሠረትን በማዘመኗ ከሰሃራ ሀገራት በታች ሦስተኛ ትልቅ ኢኮኖሚ መሆን ችላለች

Nov 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ምርት ስሌት መሠረትን በማዘመኗ (GDP Rebasing) ከሰሃራ ሀገራት በታች ሦስተኛ ትልቅ ኢኮኖሚ መሆን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላለፉት 11 ዓመታት የሀገር ውስጥ ምርት ስሌት መሠረትን ማዘመን (ሪቤዝ) ሳይደረግለት ቆይቷል።

የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት መስፈርት ኢኮኖሚዎች ቢበዛ በየአምስት ዓመቱ እንዲከለሱ የሚጠብቅ ቢሆንም፣ አዳዲስ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ለማካተትና ሚና የቀነሰውን ለማስተካከል የሚያስችል አሰራር ላለፉት 11 ዓመታት ሳይከናወን መቆየቱን አስረድተዋል።

ባለፈው ዓመት ተጀምሮ ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀውና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያሳተፈው ሰፊ የቆጠራ ሥራ በስታቲስቲክስ ኤጀንሲና በዓለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ መከናወኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ይህም ከለውጡ በኋላ በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች የተፈጠሩ አዳዲስ ተነሳሽነቶችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያለበትን ትክክለኛ ገጽታ ለመለካት እድል መስጠቱን ተናግረዋል።

በማብራሪያቸውም ከለውጡ በፊት ያልነበሩና በአዲሱ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) አለካክ ታሳቢ የተደረጉ ዘርፎችን አንስተዋል።

ከእነዚህም መካከል በትሪሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያንቀሳቅሰው የዲጂታል ኢኮኖሚ፣ የከተሞች የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ፣ በግብርና የተተገበረው የክላስተር አስተዳደርና የሌማት ትሩፋት ውጤቶች፣ እንዲሁም ቀደም ሲል በመንግሥት ስር ሦስት ብቻ የነበሩት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዛሬ በመንግሥትና በግል ከ15 በላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ ውጤቶች፣ የንፋስ፣ የግድብና የሶላር የኢነርጂ ፕሮጀክቶች፣ የቱሪዝም መሠረተ ልማቶችና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን የማስተናገድ አቅም፣ እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን ለውጦች በክለሳው ታሳቢ መደረጋቸውን አብራርተዋል።

በእነዚህ ድምር ለውጦች በተሠራው ቆጠራ፣ የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ምርት ስሌት መሠረትን ማዘመን (GDP Rebasing) ከቀረቡት ሦስት አማራጮች የመጨረሻው አማራጭ ተወስዶ 210 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ገልጸዋል።

በዚህም ከሰብ- ሰሃራ አፍሪካ ሀገራት ከደቡብ አፍሪካና ከናይጄሪያ ቀጥሎ ሦስተኛው ትልቅ ኢኮኖሚ እንዲሁም በቀጣናው ትልቁ ኢኮኖሚ መሆን መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

ሂደቱ በዓለም ባንክና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ) የቅርብ ክትትልና ድጋፍ የተሠራ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ በሀገሪቱ አሁንም በርካታ መደበኛ ያልሆነ (ኢንፎርማል) የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ቢኖርም በተቆጠረው ብቻ ይህን ደረጃ መድረስ ትልቅ ድል መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት ያጠናክራል -ምሁራን

አሶሳ፤ ህዳር 16/2019(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ለቀጣናው ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስርና የጋራ ተጠቃሚነት ጉልህ አስተዋጽ...

Nov 26, 2026

በሐረሪ ክልል ወጣቶችና ሴቶች በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በመሳተፍ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው

ሐረር፤ ህዳር 16/2019 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል ወጣቶችና ሴቶች በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በመሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢ...

Nov 26, 2026

ኢትዮጵያና ዩጋንዳ ለአፍሪካ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትና ለጋራ ዕድገት ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ያጠናክራሉ- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 15 /2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ዩጋንዳ ለአፍሪካ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትና ለጋራ ዕድገት ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር እንደሚያጠናክሩ ምክ...

Nov 25, 2026

በማህበር በመደራጀት በሌማት ትሩፋት የንብ ማነብ ስራ በመሰማራት የተሻለ ገቢ ማግኘት ችለናል -አርሶ አደሮች

ቦንጋ ፣ ህዳር 12 /2019 (ኢዜአ)፦ በካፋ ዞን ሺሾ-እንዴ ወረዳ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብሩ የንብ ማነብ ሥራ ላይ በመሰማራት የተሻለ ተጠቃሚ መሆናቸውን አ...

Nov 23, 2026