የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የአውሮፓ ዋንጫን ለበርካታ ጊዜ ያነሱት አገራት እነማን ናቸው?

Jan 13, 2025

IDOPRESS

(በሙሴ መለስ)

እ.አ.አ 1960 የመጀመሪያው የአውሮፓ ዋንጫ (በቀድሞ አጠራሩ ኢሮፒያን ኔሽንስ ካፕ) የጀመረበት ዓመት ነው።

በፈረንሳይ አስተናጋጅነት እ.አ.አ ከሐምሌ 6 እስከ 10 1960 በተካሄደው ውድድር የያኔዎቹ ሶቪየት ሕብረት፣ ቼኮዝሎቫኪያና ዩጎዝላቪያ ተሳትፈዋል።

ሶቪየት ሕብረት (በአሁኑ ስያሜዋ ሩሲያ) በፍጻሜው ጨዋታ ዩጎዝላቪያን ስላቫ ሜትሬቬሊና ቪክቶር ፖንዴልኒክ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 1 በማሸነፍ ታሪካዊውን ዋንጫ አንስታለች።

ከ64 ዓመት በፊት የተጀመረው የአውሮፓ ዋንጫ የዘንድሮውን ሳይጨምር 10 አገራት የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል።


ጀርመንና ስፔን በተመሳሳይ ሶስት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ስኬታማ የሆኑ አገራት ናቸው።

ምዕራብ አውሮፓዊቷ ጀርመን እ.አ.አ በ1972፣ 1980 እና 1996 አህጉራዊውን ክብር ከፍ አድርጋ አንስታለች።

ጀርመን ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ያነሳችው ምዕራብ ጀርመንና ምስራቅ ጀርመን ከመዋሃዳቸው በፊት ነበር።

ብሔራዊ ቡድኑ ካነሳቻው ዋንጫዎች በተጨማሪ 3 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሶ ተሸንፏል።

በደቡብ ምዕራብ አውሮፓ የምትገኘው ስፔን እ.አ.አ በ1964፣ 2008 እና 2012 በተካሄዱ ውድድሮች ዋንጫውን አንስታለች።

1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሳ ሽንፈትን አስተናግዳለች።

ስፔን በሁለት ተከታታይ የአውሮፓ ዋንጫዎች ዋንጫ ያነሳች ብቸኛ አገር ናት።

ጣልያንና ፈረንሳይ የአውሮፓ ዋንጫን ክብር ሁለቴ በመጎናጸፍ ይከተላሉ።

የደቡብ ማዕከላዊ አውሮፓዊቷ አገር ጣልያን እ.አ.አ በ1968 እና 2020 ዋንጫውን አንስታለች።


የ16ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ባለቤት ጣልያን በጀርመን አስተናጋጅነት እየተደረገ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በጥሎ ማለፉ በስዊዘርላንድ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ የሚታወስ ነው።

ሰማያዊዎቹ በሚል ቅጽል ስም በሚጠራው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እ.አ.አ በ1984 እና 2000 የአውሮፓ ዋንጫን ወስዷል።

በተጨማሪም ጣልያን 2 ጊዜ እና ፈረንሳይ 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰው ሽንፈት አስተናግደዋል።

ፖርቹጋል፣ዴንማርክ፣ ኔዘርላንድ፣ግሪክ፣ ሩሲያና በቀድሞ አጠራሯ ቼኮዝሎቫኪያ( በአሁኑ ሰዓት ቼክ ሪፐብሊክና ስሎቫኪያ የሚጠሩት አገራት) በተመሳሳይ አንድ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫን አንስተዋል።

ሩሲያ 3 ጊዜ እንዲሁም ቼኮዝሎቫኪያና ፖርቹጋል በተመሳሳይ 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰው ተሸንፈዋል።

ከዚህ ውጪ ዋንጫ ባያነሱም የቀድሞ ዩጎዝላቪያ 2፣ ቤልጂየምና እንግሊዝ በተመሳሳይ 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰዋል።

በጀርመን እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ አዲስ የዋንጫ ባለቤት ይገኝ ይሆን? ጥያቄው ሐምሌ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ምላሽ ያገኛል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026