የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

Sep 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የምግብ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካትና የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ ከተቀመጠው ስትራቴጂካዊ የግብርና ምርቶች መካከል ሩዝ አንዱና ዋነኛው ነው::

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሩዝ ልማት በሀገሪቱ የግብርና ፖሊሲ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በስፋት እየተከወነ ይገኛል::

በተለይ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ከውጭ የሚገባውን የሩዝ ምርት በአገር ውስጥ ለመተካት በተያዘው አገራዊ አቅጣጫ መሠረት ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል።


የጋምቤላ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድሩው ቱት ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ክልሉ ለሩዝ ልማት አመቺ በመሆኑ አርሶ አደሩ በዘርፉ ለመሰማራት የሚያሳየው ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል።

በተለይም በአኝዋህ እና በማጃንግ ዞኖች በሩዝ ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች አበረታች ውጤት እያገኙ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የተገኘውን አዎንታዊ ውጤት በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች በማስፋት፣ አገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት የሩዝ መፈልፈያ ማሽኖችን እና ምርታማ የሆኑ አዳዲስ የሩዝ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

እንደ ሩዝ ልማት ያሉ የተመረጡ የግብርና ኢኒሺቲቮች የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር፣ አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ በማቅረብ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረጋቸውንም አክለው ገልፀዋል።

የአቦቦ ወረዳ አርሶ አደር እስማኤል ሁሴን፤ በአካባቢያቸው ሩዝ በማልማት በሄክታር እስከ 60 ኩንታል ምርት ማግኘት መቻላቸውን ገልፀዋል።

በመሆኑም በሩዝ ልማት ዙሪያ የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል አካባቢው ያለውን እምቅ ተፈጥሮአዊ ሀብት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አርሶ አደሩ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚ እየሆነ እንደሚገኝ የገለፁት ደግሞ በዲማ ወረዳ የኮይ ቀበሌ የልማት ጣቢያ ባለሙያ አቶ ተረፈ ታፈሰ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026