🔇Unmute
በእግር ኳስ ጨዋታ ከግብ አስቆጣሪዎች ጀርባ ኳስን ፍትፍት አርገው ጨርሰው የሚያቀብሉ ተጫዋቾች አሉ።
አንድ ተጫዋች ግብ ሲያገባ ከማግባቱ ባልተናነሰ ማን ኳሱን አቀበለው? የሚለው ጥያቄ በተመልካቾች ይነሳል።
በእግር ኳስ እድገት ውስጥ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለጎል ኳስ አመቻችተው የሚያቀብሉ ተጫዋቾች ትልቅ ዋጋ ይሰጣቸዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን አሰናበተ
በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

የ33 ዓመቱ የሴኔጋል አምበል ሳዲዮ ማኔ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ካስቆጠረው አንድ ግብ በተጨማሪ ሶስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዟል።
ማኔ ሴኔጋል ለሩብ ፍጻሜ እንድታልፍ ያበረከተው አስተዋጽኦ ትልቅ የሚባል ነው።
ስምንት ተጫዋቾች በተመሳሳይ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ግቦችን አመቻችተው አቀብለዋል።

ናይጄሪያውያኑ አዴሞላ ሉክማን እና አሌክስ ኢዎቢ፣ የሞሮኮው አዝዲን ኡናሂ፣ የአልጄሪያው አኒስ ሃጂ-ሙሳ፣ የቡርኪናፋሶው ዳንጎ ኡታራ፣ የቱኒዚያው ሃኒባል ሜጅብሪ፣ የደቡብ አፍሪካው ላይል ፎስተር እና የታንዛንያ ኖቫቱስ ሞሮሺ በሁለት ግቦች ላይ እጃቸው ያለበት ተጫዋቾች ናቸው።

የናይጄሪያው የክንፍ የመስመር ተጫዋች አዴሞላ ሉክማን ሁለት ግቦችን በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አስቆጥሯል።

የኮትዲቯሩ ክርስቶፈር ኦፔሪ እና የናይጄሪያው ሳሙኤል ቹኩዌዜ በተመሳሳይ አንድ አንድ ግቦች ከመረብ ላይ እንዲቆጠሩ የቀጥታ ተሳትፎ አድርገዋል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬን (ካፍ) የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ምርጫ ላይ ካስቀመጣቸው መመዘኛ መስፈርቶች አንዱ ማን ብዙ ለጎል የሚሆን አቀበለ? የሚለው ይገኝበታል።
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እስከ ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የግብ አግቢዎችና የኳስ አቀባዮቹ ፉክክር በያዘው ግለት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
አምቦ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ለንብ ማነብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ...
Jun 14, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የበጋ መስኖ ልማት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የአርስ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን የክልሉ ምክት...
Jun 11, 2026
ሐረማያ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን እያጎለበተ እንደሚገኝ አስታወቀ። ዩኒቨ...
Jun 1, 2026
ሆሳዕና፣ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የሕብረት ሥራ ማህበራትን ደግፎ የማብቃት ሥራው ተጠናክሮ እ...
May 26, 2026