የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የአዲስ አበባ የልማት ስኬቶች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና አይቀሬነት የሚያረጋግጡ ናቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Mar 11, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ የልማት ስኬቶች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና አይቀሬነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድል ፕላዛ እና የቁርጡሜ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የስሉጥ ከተሜነት መገለጫ ለነዋሪዎች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ምቹ የአገልግሎት ምኅዳር መፍጠር መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዋናነትም የከተሜነት የአኗኗር ሥርዓት ፅዳትና ውበት የተላበሰ የአረንጓዴ ስፍራ፣ ለዜጎችና ተሽከርካሪዎች ምቹ የእንቅስቃሴና ጤናማ የመኖሪያ ምኅዳር መፍጠር ማለት እንደሆነም ገልጸዋል።


በአዲስ አበባ ቴዎድሮስ አደባባይ ለምረቃ የበቁ ፕሮጀክቶችም የአረንጓዴ፣ የወንዝ ዳርቻ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ፣ የህጻናት መጫወቻና መናፈሻዎችን አሟልቶ የተገነባ መሆኑን አስተውቀዋል።

በዚህም የድል ፕላዛ እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች ግንባታም የከተሜነት መስፈርትን በማሟላት ለመዲናዋ ተጨማሪ ድምቀት ለመሆን እንደበቁ ተናግረዋል።

የተገነቡ መሰረተ ልማቶች አካባቢውን ውብ ገጽታ በማላበስ የመሬት ውስጥ ባለሦስት ወለል ሕንጻ 500 ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል አቅም እንዳለው አስረድተዋል።

አካባቢው ውብና ማራኪ ገጽታ መላበሱም ለመዲናዋ የንግድና ቱሪዝም ልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና አይቀሬ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ ለዚህም በልማት መስክ የተፈጠረው የትብብር አቅም ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሰረት እየጣለ ነው ብለዋል።


የአዲስ አበባ አስደናቂ የልማት ስኬቶች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና አይቀሬነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የዮድ አቢሲንያ ባህል ማዕከል ባለቤት ትዕዛዙ ኮሬ በበኩላቸው፤ አዲስ አበባ ታሪክና ማንነቷን በሚገልጥ አስደናቂ የለውጥ ጉዞ ላይ ናት ብለዋል።

መንግስት ለግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የፈጠረው አስቻይ ሁኔታም የአልሚ ባለሃብቶችን ተነሳሽነትና አቅም በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት እየመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026