የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ኢትዮጵያን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ፤ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ጉዞ

May 15, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

የመደመር መንግስት የኢኮኖሚ እሳቤ የሀገራችንን ግብርና በተሟላ መልኩ ለማዘመን የሚያስችል ትልቅ ራዕይ ላይ የተመሠረተ ነው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለዘመናት ከድህነት አዙሪት መውጣት ያልቻለው የምርት ሂደቱ ከዝናብ ጥገኝነት እና ከኋላቀር አሠራር ባለመላቀቁ እንደሆነ ይታመናል ።

የግብርናው ዘርፍ ማሻሻያ ዋና ግብ የዜጎችን ክብር ከፍ የሚያደርግና ሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ እንዲሆን ተደርጓል። ለዚህም የገጠሩን ማኅበረሰብ ሕይወት ለመለወጥና ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ኢንደስትሪያላይዜሽንና የግብርና ትራንስፎርሜሽን እንደ ዋና መሠረት ተቀምጠዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግሥት የግብርናውን ኋላቀር ሂደት በመቀየር ቴክኖሎጂን እንደ ዋና ግብዓት በመጠቀም ረገድ ትልቅ የታሪክ እጥፋት ፈጥሯል። ይህም ግብርናው ከልመናና ከችሮታ ወጥቶ የኢኮኖሚው ዋና ሞተር እንዲሆን አስችሎታል። በተለይም አርሶ አደሩን ወደ ገበያ-ተኮር ምርት በማሸጋገር፣ የሥነ-ምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና ለሚሊዮኖች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በኢኮኖሚ ማሻሻያው አማካኝነት ግብርናን የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ግብዓት በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካትና ለውጭ ገበያ ጥራት ያለው ምርት ለማቅረብ ጠንካራ መሠረት ተጥሏል።

በመንግሥት የተቀናጀ ጥረት የተገኙ ውጤቶችም የሚያበረታቱ ናቸው። በ2013 በጀት ዓመት 17.2 ሚሊዮን ሄክታር የነበረው የታረሰ መሬት፣ በ2017 በጀት ዓመት ድግግሞሽን ጨምሮ ወደ 32.2 ሚሊዮን ሄክታር አድጓል። በዚህም ጠቅላላ የሰብል ምርት ከ356.6 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 836.4 ሚሊዮን ኩንታል ከፍ ብሏል። "የትኛውም መሬት ፆም አያድርም" በሚል መርህ በተከናወነ ሥራ፣ በ2017 የምርት ዘመን አጠቃላይ የግብርና ምርት 1.57 ቢሊዮን ኩንታል ደርሷል። በተለይም የስንዴ ምርት በየዓመቱ የ49 በመቶ ዕድገት በማሳየት፣ ሀገሪቱ የምግብ ሉዓላዊነቷን ከማረጋገጥ ባለፈ ስንዴን ለውጭ ገበያ ማቅረብ አስችሏታል ። ከዚህ በተጨማሪ የሩዝ ምርት ከ3 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 63 ሚሊዮን ኩንታል፣ የቡና ምርት ደግሞ ወደ 11.5 ሚሊዮን ኩንታል አድጓል።

መንግሥት በይፋ ተግባራዊ ያደረገው "የሌማት ትሩፋት" መርሃ-ግብር የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርትን በማሳደግ ረገድ ተምሳሌታዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በወተት፣ በዶሮ፣ በማርና በዓሳ ልማት የታየው ውጤት የኢኮኖሚ ነፃነትን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ድርሻ አለው። በተመሳሳይ በከተማ ግብርና ረገድ የተከናወኑ ተግባራት የከተሞችን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የጓሮ ሜዳዎችንና የሕንፃ ጣራዎችን ለምርታማነት እንዲውሉ በማድረግ የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም እና ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት መንግሥት ግብርናን ማዘመንና የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው አድርጓል። ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ማስፋፋት፣ የግብርና ፋይናንስ አቅርቦትን ማሻሻልና የግል ዘርፉን ተሳትፎ ማሳደግ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው። የመስኖ አቅምን በማጎልበት ግብርናን ከዝናብ ጥገኝነት የማላቀቅ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። እንዲሁም "ከእርሻ እስከ ጉርሻ" ያለውን የዕሴት ሰንሰለት ለማዘመን ዲጂታል ቴክኖሎጂንና ሜካናይዜሽንን በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል ታቅዷል።

መንግሥት የጀመረውን የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በማጠናቀቅ ግብዓቱን በሀገር ውስጥ ለማምረት በዝግጅት ላይ ይገኛል። ዛሬ የተመዘገቡት ውጤቶች የነገው ብሩህ ጉዞ መሠረት ናቸው። መንግሥት ኢትዮጵያን ከተረጂነት ወደ አምራችነት፣ ከምግብ ዋስትና ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማሸጋገር የገባውን ቃል በተግባር እየፈጸመ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026