🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር "ኢቲቱ" የተሰኘና ወተትን ለማርጋት የሚያስችል የፕሮ ባዮቲክ እርሾ ይፋ አደረገ።
ኢንስቲትዩቱ አዲሱን የምርምር ውጤት ይፋ ያደረገው፣የዓለም የወተት ቀንን አስመልክቶ ዛሬ በተዘጋጀ የጋራ የውይይት መድረክ እና አውደ-ርዕይ ላይ ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ እንደገለጹት፤ "ኢቲቱ" የተሰኘው አዲሱ የፕሮ ባዮቲክ እርሾ በሃገሪቱ ያሉ የወተት ማቀነባበሪያ ድርጅቶች በውጭ ምንዛሪ ከውጭ አስገብተው የሚጠቀሙበትን እርሾ የሚተካ ነው።
ይህ የምርምር ውጤት የወተት ማቀነባበሪያዎችን የውጪ ምንዛሪ ከማዳን ባለፈ፣ፓስቸራይዝድ የተደረገ ወተትን በአራት ሰዓታት ውስጥ ማርጋት እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።
ኢንስቲትዩቱ ምርምር ከሚያደርግባቸው የግብርና ውጤቶች ውስጥ ወተትና የወተት ተዋጽኦዎች ዋነኞቹ መሆናቸውን ገልጸው፤ ምርቱ ለምግብ ዋስትና እና ለጤንነት ወሳኝ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዘ መሆኑን አብራርተዋል።
ኢንስቲትዩቱ የተሻሻሉ የሰብል እና የእንስሳት ዝርያዎችን በምርምር በማውጣት ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም በወተት ምርታማነት ላይ ትኩረት ያደረጉ በባዮ ቴክኖሎጂ የታገዙ ልዩ ልዩ ምርምሮች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
የዓለም የወተት ቀን የወተት ምርት ለሥነ-ምግብ እንዲሁም ለኢኮኖሚ ያለው ፋይዳ የሚታሰብበት ሲሆን፣ ዕለቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና የግብርና ድርጅት (FAO) አማካኝነት እ.ኤ.አ በ2001 የተቋቋመ ዓለም አቀፍ ሁነት መሆኑ ይታወቃል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026