የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Jun 11, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2018(ኢዜአ)፦ በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢትዮጵያውያን ለ5 ሚሊዮን ኮደሮች ምዕራፍ ስኬት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ውድ ኢትዮጵያውያን ለ5 ሚሊዮን ኮደሮች ምዕራፍ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ!

‎በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት ተችሏል። የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች» ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርቶች 5,005,146 ሰልጣኞች ተመዝግበው ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀዋል። ይህ ስኬት የሕዝባችንን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ ነው።

‎በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው። እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተሰነቀውን ግብ ለማሳካት፥ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

‎ለወጣት ተማሪዎቻችን፤ መጭው የክረምት ወቅት ትልቅ ዕድላችሁ ነው። ጊዜያችሁን በዋዛ ከማሳለፍ ተቆጥባችሁ፤ በመመዝገብና በመማር ወደ ትምህርት ገበታችሁ ስትመለሱ ተማሪዎች ብቻ ሳትሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላችሁ የዲጂታል መሪዎች እንድትሆኑ አሳስባለሁ። ሥልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጡ ሲሆን፥ የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ነው።

‎የምትገነቡት ነገ የሚጀምረው ዛሬ ነው!

‎ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ:

‎ethiocoders.et/

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026