የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የጉባ ብስራቶች -የኢትዮጵያ የማከናወን ጉዞ ቀጣይነት ማሳያዎች

Jun 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Homegrown Economic Reform) መዋቅራዊ ማነቆዎችን በመስበር ረገድ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁ በተበሰረበት ታሪካዊ ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ያደረጓቸው "የጉባ ብስራቶች" ሀገሪቱ በኃይል፣ በኢንዱስትሪ፣ በአቪዬሽን፣ በማዕድንና በከተማ ልማት ዘርፍ የደረሰችበትን ከፍተኛ የማስፈጸም አቅም ያሳዩ ሲሆን፣ እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች "ኢትዮጵያ ታከናውናለች" የሚለውን አገራዊ መርህ በተግባር የሚያረጋግጡ ናቸው።

ለጉባ ብስራቶች ዋነኛ ምሰሶ የነበረውና ለመላው አፍሪካ ኩራት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ፍጻሜ ማግኘቱ የሪፎርሙ ውጤታማነት ትልቁ ማሳያ ነው።

የለውጡ መንግስት የፋይናንስ ማነቆዎችን በቁርጠኝነት በመፍታት እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በመቋቋም ግድቡን አጠናቅቆ ሌላ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጀምሯል። ይህም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ አንዱ የታሪክ እጥፋት ነው።

ኢትዮጵያ የወደፊት የኃይልና የቴክኖሎጂ ፍላጎቷን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የኒውክሌር ኃይልን ለሰላማዊ አገልግሎት ለማዋል የጀመረችው ታሪካዊ ጉዞ ሌላኛው ደማቅ ብስራት ነው።

በሪፎርሙ ወቅት ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር የተደረጉት ስምምነቶችና የተጀመሩት የዝግጅት ስራዎች፣ ሀገሪቱ በሕክምና፣ በግብርና እና በኃይል አማራጮች ላይ ያላትን የረጅም ጊዜ አርቆ አሳቢነትና የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ሽግግር ቁርጠኝነት ያሳያሉ።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያን የአቪዬሽን መሪነትና የኮሜርስ የበላይነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስቀጠል የታለመው የአዲሱ የቢሾፍቱ ሜጋ አየር ማረፊያ (Bishoftu International Airport) በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።

ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት ከ110 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን ግዙፍ የጭነት አውሮፕላኖችን ለማስተናገድ የተነደፈው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ሀገሪቱን የአፍሪካ ዋና የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ መገናኛ ኮሪደር የማድረግ ስትራቴጂ አካል ነው።

ከዚህ በተጨማሪ በማዕድን ዘርፍ ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረውን አገራዊ እምቅ አቅም ወደ ጥቅም ለመቀየር በኦጋዴን ተፋሰስ የተገነባው የተፈጥሮ ጋዝ ፋብሪካ ተጠናቆ በስኬት ተመርቋል።

ይህ ሜጋ ፕሮጀክት ሀገሪቱ የራሷን የሃይልና የኢንዱስትሪ ግብዓት እንድታመርት አቅም የፈጠረ ሲሆን፣ ለሀገር ውስጥ የኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ የሪፎርሙ ታላቅ ስኬት ነው።

የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት በዘላቂነት ለማረጋገጥና በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገባውን ግብዓት በሀገር ውስጥ ለመተካት የግዙፍ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።

ይህ ፕሮጀክት አርሶ አደሩን ከውጭ አቅራቢዎች ጥገኝነትና ከተደጋጋሚ የእጥረት አደጋዎች የሚታደግ ከመሆኑም በላይ፣ የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የተነደፈ ስልታዊ የሪፎርሙ አካል ነው።

ኢትዮጵያ በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያላትን የውጭ ምንዛሬ ጫና ለማቃለልና የኢነርጂ ዋስትናዋን ለማጠናከር የጀመረችው የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ሌላኛው ስትራቴጂካዊ የጉባ ብስራት ነው።

በከተማ ልማትና በዜጎች የኑሮ ደረጃ መሻሻል ረገድ ትልቁ አገራዊ ንቅናቄ የሆነው የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት በከፍተኛ ፍጥነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ጭምር እየተተገበረ ይገኛል። ይህ ፕሮጀክት የቤት ተደራሽነትን ከማሻሻሉም በላይ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድልና የእውቅት ሽግግር ለመፍጠር ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው።

በአጠቃላይ የጉባ ብስራቶች ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጉዞ ውጤታማነትን የሚያመላክቱና ኢትዮጵያ ለቀጣዩ ትውልድ ዘላቂ ብልጽግናንና የኢኮኖሚ ነፃነትን የሚያረጋግጥ ታሪካዊ መሰረት እየጣለች ለመሆኑ ህያው ምስክሮች ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026