የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ዘንድሮ ከዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ቱሪዝምና ከውጭ ጎብኚዎች ከአምስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል

Jul 1, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2018 (ኢዜአ)፡- ዘንድሮ ከዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ቱሪዝምና ከውጭ ጎብኚዎች ከአምስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት 204 ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን አስተናግዳለች ብለዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር" በሚል ርዕስ የቱሪዝም ዘርፉን በተመለከተ ከኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።


በቆይታቸውም በብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ትኩረት ተሰጥቶት ኢንቨስት የተደረገበት የቱሪዝም ዘርፍ ልክ እንደ ግብርናውና ኢንዱስትሪው ሁሉ ከፍተኛ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።


ዘንድሮ ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ኢትዮጵያን የጎበኙ ሲሆን፤ ይህም ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ100 ሺህ፣ ከ2016 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር ደግሞ ከ300 ሺህ በላይ ጎብኚዎች ብልጫ አሳይቷል ነው ያሉት።


ከዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ከውጭ የቱሪስት ፍሰት (ማይስ) በአጠቃላይ ከአምስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ መገኘቱ የሚያሳየው ቱሪዝም ውጤት እያመጣ መሆኑን ነው ብለዋል።


የሀገር ውስጥ ቱሪዝም መነቃቃቱን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዘንድሮ ከ50 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥ ተንቀሳቅሰው የተለያዩ መዳረሻዎችን መጎብኘታቸውን ጠቅሰዋል።


ይህም ከአምናው የአንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን፣ ከከቻአምናው ደግሞ የዘጠኝ ነጥብ አራት ሚሊዮን ጎብኝዎች ብልጫ አለው ነው ያሉት።


በዚህም 79 ቢሊየን ብር ገቢ በሀገር ውስጥ ቱሪዝም መሰብሰቡን ተናግረዋል።


ኢትዮጵያ ውስጥ ዘንድሮ 204 ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች የተካሄዱ ሲሆን፣ ይህም ከሁለት ዓመት በፊት ከነበረው በ166፣ ከአምናው በ50 ጉባኤዎች ብልጫ አለው ብለዋል።


የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ተሳታፊዎች በየዓመቱ እያደገ መምጣቱን በማንሳት፤ በዚህ ዓመት በተካሄዱ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች 166 ሺህ ሰዎች መሳተፋቸውን ነው ያነሱት።


በዘርፉ ከፍተኛ ዕድገት እየመጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ኮንፈረንስ ማድረግና በቡድን መጎብኘት እየጨመረ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026