የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ199 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የጠጠር መንገዶች ተገንብተዋል

Jul 18, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረ ብርሃን ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ199 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 72 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ መገንባቱን የዞኑ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ መምሪያ ገለጸ።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ ለኢዜአ እንደገለጹት፤የተገነቡት አዲስ የጠጠር መንገዶች የመንገድ ተደራሽነት ባልነበረባቸው 11 ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ ነው፡፡

የመንገድ ግንባታው በአገረ ማሪያም ከሰም ወረዳ ቅዱስጌ ከሰም፤በመርሐቤቴ ወረዳ ከዋና መንገድ ሐና ቤተክርስቲያን፤ በሞረትና ጅሩ ዲላሞ ቀበሌን ጨምሮ 11 ወረዳዎች መካሔዱን ጠቅሰዋል፡፡


የተገነቡት መንገዶች ክረምት ከበጋ 42 ሺህ ለሚደርሱ የአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት የሚችሉ መሆኑን ገልፀዋል።

የመንገዶቹ መገንባት በዞኑ 3 ሺህ 346 ኪሎሜትር የነበረውን ሽፋን ወደ 3 ሺህ 421 ኪሎሜትር የሚያሳድግ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በበጀት ዓመቱ ከመንገድ ግንባታው ጎን ለጎን የተለያዩ የድልድይ ግንባታ ስራዎች መከናወናቸውን ነው አቶ ደጀኔ የገለጹት።

ለመንገድ ግንባታው ወጪ የተደረገው ከ199 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ በክልሉ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን የማሕበረሰቡ ተሳትፎም ከፍተኛ እንደነበር ገልፀዋል።


በመንገድ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ለ7 ሺህ 522 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፈጠሩንም አክለው አብራርተዋል፡፡

የተገነቡት መንገዶች የአርሶ አደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር የጎላ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026